የፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ አጭር የህይዎት ታሪክ
ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ ወልደማርያም ታህሳስ 22 ቀን 1953 ዓ.ም በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮ ከተማ ከአባታቸው ከአቶ ሳህሌ ወልደማርያም እና ከእናታቸው ከወ/ሮ ብዙአለም ብርሀኑ ተወለዱ፡፡

እድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ• የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በባኮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት፤ ምዕራብ ሸዋ• ሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በእንጦጦ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት፤ አዲስ አበባ• የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪያቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ• ሶስተኛ ዲግሪያቸውን በሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ አጠናቀዋል፡፡
የፕሮፌሰር ሳሙኤል የስራ ልምድ• ኮረም ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት• ሆጤ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመምህርነት እና በሀላፊነት፤• ጎንደር መምህራን ኮሌጅ በመምህርነት እና በሀላፊነት፤• እንዲሁም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተቀጠሩበት ከነሀሴ 01/2002 ዓ.ም ጀምሮ ህይዎታቸው እስካለፈበት ድረስ በመምህርነት፣ በተመራማሪነት እና በሀላፊነት ያገለገሉ ሲሆን የፕሮፌሰርነት ማዕረጋቸውን በነሀሴ 12/2011 ዓ.ም አግኝተዋል፡፡
የፕሮፌሰር ሳሙኤል የሰሩባቸው የተለያዩ የሀላፊነት ቦታዎች • በሆጤ ከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ት/ክፍል ሀላፊነት፤• በጎንደር መምህራን ኮሌጅ አካዳሚክ ም/ዲን፤• በጎንደር ዩኒቨርስቲ በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ፕሮግራም አስተባባሪ • እንዲሁም ህይዎታቸው እስካለፈበት ቀን ድረስ የዩኒቨርሲቲው የድህረ – ምረቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በመሆን አገልግለዋል፡፡

ፕሮፌሰር ሳሙኤል• በተለያዩ ውጭ ሀገራት አጫጭር ስልጠናዎች ወስደዋል፡፡
ፕሮፌሰር ሳሙኤል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ያበረከቷቸው ዋና ዋና አስተዋፅኦዎች• በርካታ የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎችን አስተምረውና አማክረው አስመርቀዋል፡፡• የ2ኛ እና የ3ኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በሙያቸው ከስራ ባለደረቦቻቸው ጋር በመሆን እንዲከፈቱ የበኩላቸውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል፡፡• በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች እየተጋበዙ የድህረ- ምረቃ ተማሪዎችን ያስተምሩ እና ይፈትኑ ነበር፡፡• ሁለት የአዕምሮ ንብረት ባለቤትነት ከኢትዮያየ አእምሯዊ ንብረት ጥበቃ አግኝተዋል፡፡ እነርሱም- ከዳጉሳ ሰብል ቢራ መጥመቂያ ዘዴ እና- ፓርትኒየም የተሰኘውን አረም ማጥፊያ ዘዴ ናቸው፡፡
ፕሮፌሰር ሳሙኤልባለትዳርና የሁለት ሴት ልጆች አባት ሲሆኑ ፣ የልጅ ልጆችም አፍርተዋል። እኒህ ታላቅ ሰው ከመስከረም 01/1976 ዓ.ም ጀምረው እስከ ዛሬዋ ዕለት በአጠቃላይ ለ37 አመታት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ፣ ለቤተሶቻቸው ጊዜ ሳይሰጡ፣ ሁሌም ጊዜቸውን በሥራ በማሳለፍ ሲሠሩ ቆይተዋል።
ሆኖም ባደረባቸው ህመም ምክንያት በተወለዱ በ59 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡ የቀብር ሥነ- ስርዓታቸውም ዛሬ ነሐሴ 30/2012 ዓ.ም በደብረ-ሰላም ቀራንዮ ኪዳነ-ምህረት የጎንደር ዩኒቨርሲቲና የጎንደር መምህራን ኮሌጅ ማህበረሰብ እንዲሁም ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት ተፈፅሟል፡፡
ለቤተሰብ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናት እየተመኘን ነብሳቸውን በዓፀደ-ገነት ያኑርልን!የሕዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትጎንደር ዩኒቨርሲቲ




