የ2011 ዓ.ም እጩ ተመራቂ ተማሪዎች በደማቅ ሁኔታ ተመረቁ
በዚህ ዓመት ዩኒቨርስቲያችን በመደበኛው፤ በተከታታይና በክረምት መርሀ ግብሮች በአጠቃላይ ወንድ 30,501 ሴት 17,222 አጠቃላይ ድምር 47,723 ተማሪዎችን በማስተማር ላይ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል በ2011 ዓ.ም 5,138 ወንድና 3,227 ሴት በድምሩ 8,365 ተማሪዎች በመጀመሪያ፤ በሁለተኛ እና በሶስተኛ ድግሪ (247 የሥነ ማስተማር ዘዴ ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ የዩኒቨርሲቲው መምህራንን ጨምሮ) ሰኔ 29/2011ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ አስመርቋል፡፡ ይህ የምረቃ ፕሮግራም እጥር ምጥን ያለና እጅግ ያማረ እንደነበር በዕለቱ ተገኝተን ለማረጋገጥ ችለናል፡፡
በምረቃ ፕሮግራሙ የታደሙ የክብር እንግዳ የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባና ሌሎች ከፌደራልና ከክልል የመጡ እንግዶች በማግስቱ ሰኔ 30/2011ዓ.ም የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶላቸው የዩኒቨርሲቲውን የተለያዩ ግቢዎች ጎብኝተዋል፡፡ በመጨረሻም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የሆኑትን ዶ/ር አስራት አጸደወይንን ጨምሮ ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችና የክብር እንግዶች በማራኪ ግቢ በስማቸው ችግኝ በመትከል ጉብኝታቸውን አጠናቀዋል፡፡
ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



