ዩኒቨርሲቲዎችን ያሳተፈ የኮቪድ -19 መከላከልና መቆጣጠር እንዲሁም የማህበረሰብ አቀፍ ጤና መድህን ተግባራት የንቅናቄ መድረክ ታህሳስ 19/2013 ዓ.ም በባሕርዳ ከተማ ተካሄደ
በመድረኩ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር፣ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የጎንድር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይንን ጨምሮ ሌሎች የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የዞንና የወረዳ የጤና ተቋማት መሪዎችና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።
በዚህ የንቅናቄ መድረክ በክልሉ ጤና ቢሮ በኩል በኮቪድ-19 መከላከልና መቆጣጠር ላይ አጠቃላይ የተከናወኑ ተግባራት በሪፖርት ቀርበው ተገምግመዋል። ግምገማው ያተኮረው በኮቪድ-19 ላይ ሲሆን በማህበረሰቡ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ መዘናጋት እየታየ በመሆኑ የዘመቻ ሥራ እደሚያስፈልግ ተገልጿል።
በኮቪድ-19 መከላከል ላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ሁሉም የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ያበረከቱት አስተዋፅዖ ከፍተኛ በመሆኑ ያከናወኗቸውን ተግባራት በኢግዚቪሽን አቅርበዋል።
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲዎቹ ላበረከቱት አስተዋፅዖ የጤና ሚኒስትሯ በተገኙበት በክልሉ የተዘጋጀ የምሥጋናና የእውቅና ሽልማት የተበረከተ ሲሆን በሽልማት ሥነ – ሥርዓትቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቀዳሚ ተሸላሚ ሆኗል።
***********************
ሐገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጎንደር ዪኒቨርሲቲ







