ድህረ ምረቃ ፕሮግራምን ስለማስፋፋት አገር አቀፍ ወርክሾፕ ተካሄደ
የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለማጠናከር ዓላማ ያደረገ አገር አቀፍ ወርክሾፕ ከ ነሐሴ 3-4/2011 ዓ.ም ድረስ በዩኒቨርሲቲው ሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሄደ፡፡
በወርክሾፑ ዶ/ር ሳሙኤል ሳህሌ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ሲያደርጉ፤ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደወይን ወርክሾፑን በንግግር ከፍተዋል፡፡
ቀጥሎም የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን ለማስፋት የተግባር ስትራቴጂዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚል ርዕስ በዶ/ር ብስራት ምስጋናው ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ የ3ኛ ዲግሪ ስልጠና ሂደት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የጤና አጠባበቅ ኢንሲቲቲዩት ልምድ በኢኒስቲቲዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ካሳሁን ዓለሙ፣ በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች አተገባበር የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ልምድ በዶ/ር ብርሌው በላይነህ፣ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን የመምራትና የማስኬድ የምዕራባዉያን ልምድ በአቶ ገበየሁ በጋሻው በሳይኮሎጂ ረዳት ፕሮፌሰር ፣ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሂደት የሀሮማያ ዩኒቨርሲቲ ልምድ በዶ/ር ፍቅረ ዩሃንስ ገዳሙ ከሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ፣ የማናሽ ዩኒቨርሲቲ (ማሌዢያ) የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ሂደት ልምድ በዶ/ር ተስፋሁን መለሰ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኢንስቲቲዩት የሄልዝ ኢንፎርማቲክስ ረዳት ፕሮፌሰር እና እንደ ድህረ ምረቃ ተማሪ ግንኙነቶችን ስለመፍጠር በአሜሪካና ካናዳ ስለነበራቸው ልምድ በአቶ ሞላልኝ በላይ የ3ኛ ዲግሪ ተማሪ ከላይ የተገለጹትን ጽሁፎች አቅርበዋል፡፡
ከዚያም በአራት ትይዩ መድረኮች ሙያዊ ውይይቶች በዛሬው ዕለት ተካሂደዋል፡፡ ከውይይቱ የተያዙ ጠቃሚ ሃሳቦች በሁለተኛው ቀን በየቡድኑ ለጠቅላላ የኮንፈረንሱ ታዳሚዎች በነገው ዕለት ቀርበው ሰፊ ውይይት ከተካሄደበት በኋላ የወደፊት አቅጣጫ በማስቀመጥ ኮንፈረንሱ እንደኒጠናቀቅ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



