ድጋፍ4 #covid19

በሬድ ፎክስ መኖሪያ ግቢ የሚኖሩ 84 የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሃምሳ ሺህ ብር (50,000 ብር) በማዋጣት በማራኪ ክፍለ ከተማ ሳሙና በር ቀበሌ ለሚኖሩ 47 የተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ፡፡

ድጋፍ የተደረገላቸው በኮረና ቫይረስ ስጋት የዕለት ገቢያቸው የተቋረጠባቸውና አጋዥ የሌላቸው አቅመ ደካሞችና ቤተሰብ አስተዳዳሪዎች ናቸው፡፡ የፋሲካን በዓል በደስታ እንዲያሳልፉ ለእያንዳንዳቸው 20 ኪ.ግ ፊኖ ዱቄት፣ 3 ሊትር ዘይት፣ሁለት መቶ ብር (200 ብር) እና 6 ሳሙና እንዲደርሳቸው ተደርጓል፡፡
አትርፎ የሚደፋ እንዳለ ሁሉ ሳይበላ የሚያድር መኖሩን እንገነዘባለን፡፡ በመሆኑም ያለንን ተካፍለን እንኑር፡፡ የፈተናው ጊዜ ያልፋል፡፡
መልካም የትንሳኤ በዓል ይሁንልን፡፡

ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት
ሚያዚያ 08/2012 ዓ.ም



