ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለአንበጣ መከላከያ የሰጠውን ድጋፍ ርክክብ ፈፀመ
ዩኒቨርሲቲያችን የበረሃ አንበጣ ለተከሰተባቸው የአማራ ክልል ዞኖች አንድ ሚሊዬን ብር ድጋፍ መወሰኑን ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡በመሆኑም የሰብል መሰብሰቢያ ቁሳቁሶችና ፀረ ተህዋስያን ኬሚካል መርጫ መሳሪያ ገዝቶ በትናንትናው ዕለት ርክክብ ፈፅሟል፡፡ የድጋፍ ርክክቡን የፈፀሙት የጎንደር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መርሻ ጫኔ ሲሆኑ በክልሉ በኩል የአራቱ ዞን ግብርና መመሪያ ኃላፊዎች ናቸው፡፡ የሰሜን ወሎ ግብርና መምሪያ ኃላፊ በወልድያ፣ የደቡብ ወሎ ግብርና መምሪያ ኃላፊ በደሴ፣ የኦሮሚያ ልዩ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ በከሚሴ እንዲሁም የሰሜን ሸዋ ዞን ግብርና መምሪያ ኃላፊ በደብረ ብርሃን ተገኝተው የተደረገለቸውን ድጋፍ ተቀብለዋል፡፡ ሀገራችን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!**************************************
ህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ጥቅምት 11 /2013 ዓ.ም




