
ጥበበ ህይዎትን (ባዮ-ቴክኖሎጅን) የተመለከተ ሀገራዊ ውይይት ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባዮ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የ ‘ጥበበ ህይዎት’ን (የባዮ-ቴክኖሎጅን) ፋይዳ ቀድሞ በመረዳት በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የዘርፉን (የባዮ ቴክኖሎጅን)ትምህርት ክፍል በመክፈት ፈር ቀዳጅ መሆኑ ይታወሳል፡፡ ኢንስቲትዩቱ በጥበበ ህይወት መስክ የማህበረሰቡን ችግር በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምሮች ለመፍታት ልክ እንደ አንድ የልህቀት ማዕከል(Center of Excellence) ሁኖ እያገለገለም ይገኛል፡፡
በመሆኑም የግብርናውን ዘርፍ ለማዘመንና ምርታማነትን ለማሳደግ ዓላማ አድጎ የሚሰራውን ኦ.ፋ.ብ (OFAB /Open Forum for Agricultural Biotechnology) የተሰኘው ድርጅትን በተመለከተ ሀገራዊ የውይይት መርሀ ግብር ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ሰኔ 26/2013 ዓ.ም በአጼ ቴወድሮስ ግቢ ድህር ምረቃ አዳራሽ አካሂዷል፡፡ (የጎንደር ዩኒቨርሰቲ የዚህ ድርጅት የሰሜን ምዕራብ ኖድን በመምራት ሀላፊነት ወስዶ እየሰራ ይገኛል፡፡)

የዩኒቨርሰቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አጸደወይን፣ የዩኒቨርሰቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ ዲኖች፣ መምህራን፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሰቲዎችና ተቋማት የመጡ ባለድርሻ አካላት መርሀ ግብሩን ተሳትፈዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሰቲ በባዮ ቴክኖሎጅ ትምህርት ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር በኩል ቀዳሚ እንደነበር በመክፈቻ ንግግራቸው ያወሱት ዶ/ር ካሳሁን ዘርፉ በተለይም የግብርናውን መስክ በሳይንሳዊ ጥናትና ምርምር በማገዝ ለማሳደግ አንታዊ ሚና ይኖረዋል ብለዋል፡፡

ዶ/ር አስራት በበኩላቸው አብይ ንግግር (keynote speech) አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም ጥበበ ህይወት አሁን ላለንበት ዘመን አስፈላጊ የሆነ የትምህርት ዘርፍ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ስለሆም ዩኒቨርሰቲው በኢንስቲትዩቱ ለሚከናወኑ ስራዎች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራም በፕሬዚዳንቱ ተገልጿል፡፡

በኦ.ፋ.ብ (OFAB) የተከናወኑ ስራዎችና የወደፊት እቅዶች በኢንስቲትዩቱ ዳይሮክተር በፕ/ር ነጋ ብርሀን ቀርቧል፡፡ የቀረበውን ገለጻ መነሻ ያደረገ ውይይት ተደርጓል፡፡ የወደፊት አቅጣጫዎችም ተቀምጠዋል፡፡
ከግብርና ጋር የተያያዘ የቻይና ሀገር የባዮ ቴክኖሎጂ ተሞክሮ ቀርቧል፡፡
በመጨረሻም ኢንስቲትዩቱ የራሱን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድና የ 2014 ዓ.ም ዓመታዊ ዕቅድን አስተዋውቋል፡፡
