2011 FTA NEW Audit REPORT
ኦዲት ተደራጊ፡-……….. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
ኦዲት የተደረገዉ የበጀት ዓመት ……….2010
ኦዲት አድራጊዉ መ/ቤት………………የዋና ኦዲተር መ/ቤት
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 1 ያለአግባብ የተከፈለ ደመወዝ | የዩኒቨርሲቲው አንድ መምህር የወር ደመወዛቸው ብር 10,470.00 ለሶስተኛ ዲግሪያቸው ለመማር ወደ ቻይና ሀገር በቀን 01/01/2010 የሄዱ ሲሆን ከሄዱበት ቀን ጀምሮ ግማሽ ደመወዝ መከፈል ሲገባው አላግባብ ሙሉ ደመወዛቸውን ከሄዱበት ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 30/2010 ዓ.ም ድረስ የተጣራ ክፍያ በብልጫ ለሰራተኛው የተከፈለ መሆኑ | ብር 5,380.00 |
| ስጋት | የመንግስት ገንዘብ ያለ አግባብ ለብክነት ይዳረጋል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | የተከፈለው ክፍያ አግባብነት የሌለው በመሆኑ ገንዘቡ ተመላሽ ተደርጎ ሪፖርት ሊቀርብ ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | ለመምህሩ በብልጫ የተከፈለዉ ገንዘብ እየተመለሰ በመሆኑ ቀሪዉ ሂሳብ የሚሰበሰብ ይሆናል፡፡ | የተገኘዉ ብር 5,380.00 ሙሉ በሙሉ ተሰብስቧል |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 2 መመሪያ የጣሰ የዉሎ አበል ክፍያ | በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ከ28/06/2010-01/07/2010 ባሉት ቀናት ውስጥ በተካሄደው ስልጠና ላይ ለተሳተፉት የፋርማሲ ክፍል ባለሙያዎች የምሳ አበል የተከፈላቸው ሲሆን ክፍያው ከላይ የተገለጸውን መመሪያ በመጣስ ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን በኦዲቱ ተረጋግጧል፡፡ | ብር 23,487.80 |
| ስጋት | የተፈጸመዉ ክፍያ መንግስት ያስተላለፈዉ መመሪያ ከመጣሱም በላይ የመንግስት ገንዘብ እንዲባክን በር ሊከፍት ይችላል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | አላግባብ ከመመሪያ ውጪ የተከፈለው ክፍያ አግባቢነት የለለው በመሆኑ ገንዘቡ ተመላሽ ተደርጎ ሪፖርት ሊቀርብ ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | የዉሎ አበል መመሪያዉ የሚፈቅድ በመሆኑ ገንዘቡ ተመላሽ ሊሆን አይገባም፡፡ | በዉሎ አበል አከፋፈል ዙሪያ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ማብራሪያ እንዲሰጥ ተጠይቋል፣ |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 3 በጀት ዓመት ያልጠበቀ ክፍያ | በአጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሆስፒታሉ ከጎንደር መድሀኒት ፈንድ ኤጀንሲ በ2009 ግዥ የተፈጸመ ቢሆንም ክፍያዉ ያለበጀት አመቱ ክፍያ ተፈጽሞ ተገኝቷል፡፡ | ብር 1,619,678.26 |
| ስጋት | ወጭዎች በበጀት ዓመታቸዉ ክፍያ የማይፈጸም ከሆነ በዩኒቨርሲቲዉ ላይ የበጀት ዕጥረት ሊያስከትል ይችላል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | ለወደፊቱ ተመሳሳይ ችግር እንዳይፈጠር ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | ለመድኃኒት በጀት የተመደበዉ በቂ ባለመሆኑ እና የወቅቱ የገበያ ዋጋ ተጽዕኖ ስለነበረዉ መድኃኒቱ ገቢ ሆኖ ለህብረተሰቡ አገልግሎት መስጠት ስለነበረበት የተፈጸመ ክፍያ መሆኑን |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 4 ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ኢንተርፕራይዝ የተፈጸመ የግብዓት ግዥ | በአዋጁ መሰረት የጃንተከል ማተሚያ ኢንተርፕራይዝ የራሱን ወጪ በራሱ ገቢ እንዲሸፍን ማድረግ ሲገባዉ አላግባብ ከመደበኛ በጀት ክፍያ የተፈጸመ መሆኑን፣ | በዋና ግቢ ብር 95,583.40 በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ ብር 258,750.00 |
| ስጋት | ለኢንተርፕራይዙ በራሱ ወጭዉን ሊሸፍን ሲገባ ከመንግስት በጀት ያለአግባብ ክፍያ ሊፈጸም ይችላል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | ገንዘቡ ከኢንተርፒራይዙ ተመላሽ በማድረግ ወደ መደበኛ በጀት ገቢ ተደርጎ ሪፖርት ሊቀርብ ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | ገንዘቡ በተሰብሳቢ የተመዘገበ ሲሆን አስመልሰን ሪፖርት እናደርጋለን፡፡ |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 5 የተሰብሳቢ ሂሳብ | በበጀት ዓመቱ መጨረሻ በተሰብሳቢ ሂሳብ ሪፖርት ከተመለከተው ሂሳብ ውስጥ በጊዜ ገደቡ ያልተወራረደና ከ1 ወር እስከ 10 ዓመት በተሰብሳቢነት የቆየ መገኘቱ | ብር 114,611,493.89 |
| ስጋት | በቅድመ ክፍያ ወጭ የተደረገዉ ሂሳብ በወቅቱ ካልተወራረደ ሂሳቡ ወደ ማይወራረድበት ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | ተሰብሳቢ ሂሣቦች በወቅቱ እንዲወራረዱ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራሩ አፋጣኝ እርምጃ መውሰድ ይኖርበታል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | በተሰብሳቢነት የሚታዩት ገንዘቦች ከ 90 ሚሊየን ብር በላይ ከመንግስት ተቋማት የሚፈለግ መሆኑን በመግለጽ ተሰብስቦ ሪፖርት እንደሚቀርብ ምላሽ ሰጥቷል። |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 6 የተከፋይ ሂሳብ | በሰኔ 30/2010 ዓ.ም በተከፋይ ሂሳብ የሚታይ በግዜ ገደቡ ያልተከፈለ ሂሳብ መገኘቱ በሰኔ 30/2010 ዓ.ም የተከፋይ በተከፋይ ሂሳብ የሚታይ በግዜ ገደቡ ያልተከፈለ ሂሳብ መገኘቱ | ብር 29,508,550.00 |
| ስጋት | ዩኒቨርሲቲዉ በበጀት ዓመቱ ለመስራት ያቀደዉን በመተዉ ከባለፈዉ ዓመት የዞረዉን ዕዳ በመክፈል በዕቅድ አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይፈጥርበታል፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | ዩኒቨርሲቲው ያለበትን ዕዳ በመክፈል ከዕዳ ነጻ መሆን ያለበት ሲሆን ለወደፊቱ ክፍያዎች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲከፈሉ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | ዕዳዎችን ክትትል በማድረግ በመክፈል ላይ የመንገኝ ሲሆን ሌሎች ተከፋዬችንም ለመክፈል በክትትል ላይ እንገኛለን፡፡ |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 7 ከበጀት በላይ የተፈጸመ ክፍያ | ከበጀት በላይ እና ከበጀት በታች ሥራ ላይ የዋለ በጀት መኖሩ | ከበጀት በላይ ብር 29,063,652.11 ብር 30,208,292.46 ሥራ ላይ ያልዋለ በጀት |
| ስጋት | · ዓመታዊ ዬኒቨርሲቲዉን የስራ ዉጤት ዝቅ ያደርገዋል፡፡ · በሌሎች መ/ቤቶች ሊሰራበት የሚችለዉን በጀት በዩኒቨርሲቲዉ ስም ተይዞ እንዲቆይ ያደርጋል፡፡ · ከበጀት በላይ መጠቀም ተጠያቂነትን ያስከትላል፡፡ |
|
| የማሻሻያ ሃሳብ | ዩኒቨርሲቲው የተፈቀደለትን በጀት በመንግስት የፋይናንስ አዋጅ መሰረት በስራ ላይ እንዲያውል፤ ከተፈቀደዉ በጀት በላይ ወጪ እንዳይሆን የተቋሙ ሥራ አመራር በበጀት አጠቃቀም ላይ ተገቢውን ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ይኖርበታል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | በዩኒቨርሲቲዉ የተለያዩ የስራ ክፍሎች የሰዉ ኃይል ዕጥረት በመኖሩ ተጨማሪ ሰዓት በማሰራታችን በአንዳንድ ግዥዎች የዋጋ ጭማሪ በመታየቱ የምግብ ግብዓት ከተፈቀደዉ በጀት በላይ በመሆኑ የተከሰተ መሆኑን |
| የኦዲት ግኝትና መግለጫ | ጉዳዩ ሁኔታ ውጤት | መረጃ |
| ግኝት 8 የንብረት አያያዝና አጠባበቅ | · በቋሚ እቃ ግምጃ ቤት ዉስጥ የሚወገዱ የተለያዩ እቃዎች ተለይተዉ አለመቀመጥ · ንብረቶች ገቢ ተደርገዉ ያለምንም አገልግሎት ከሁለት አመት በላይ ተከማችተው የተቀመጡ መሆናቸው · ቢን ካርድ እና እስቶክ ካርድ የተጀመረ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ላይ ያልዋለ መሆኑ · ገቢ ተደርገዉ ከሁለት አመት በላይ የሆናቸዉ አዳዲስ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች እና ልብሶች ያለምንም አገልግሎት ተከማችተዉ የተገኙ መሆናቸዉ |
|
| ስጋት | · ንብረቶች ለበለጠ ጥፋት ይጋለጣሉ፡፡ | |
| የማሻሻያ ሃሳብ | · ዩኒቨርሲቲው የንብረት አቀማመጥ፣ አያያዝ፣ አጠባበቅና አወጋድ በመመሪያዉ መሠረት ተግባራዊ የሚደረግበት አሰራር ሊፈጠር ይገባል፡፡ | |
| የሥራ አመራሩ ምላሽ | · ያለዉ የቋሚ ዕቃ ግ/ቤት አንድ በመሆኑ ሁሉም ንብረቶች የሚከማቹበት መሆኑን · የሚሰራጩ ንብረቶች በመጠባበቂያነት የተያዙ በመሆኑ ወደፊት የሚሰራጩ መሆኑን · የመጠቀሚያ ጊዚያቸዉ ያለፈባቸዉ ንብረቶች የሚወገዱ መሆኑን |
ያዘጋጀዉ………. ……. ያጸደቀዉ……………….
ፊርማ………………. … ፊርማ……………………
ቀን…………………….. ቀን………………………



