በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፒኤች ዲ ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት ወርክሾፕ ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጥር 7/2008 ዓ.ም በታዬ በላይ ሆቴል በPHD ፕሮግራሞች መስፋፋት ላይ የልምድ ልውውጥ ወርክሾፕ አካሂዷል፡፡ ወርክሾፑን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ በዩኒቨርሰቲው ሶስት የ PHD ፕሮግራሞችና ሁለት የስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች አሁን እየተሰራባቸው ያሉ መሆኑን እና ሌሎች ወደ ስራ ያልተገባባቸው በሂደት ላይ ያሉትን የ PHD ፕሮግራሞች ገልፀው ይህ ጅማሮ ዩኒቨርሲቲያችን ከጊዜ ወደ ጊዜ ማደጉን ያመላክታል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም የ PHD ፕሮግራሞችን ለማስፋፋት በእንግድነት የተጋበዙት ምሁራን በሚያቀርቡት ጥናታዊ ፅሁፍ ከፍተኛ ልምድ የምናገኝበት ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳነት የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
በወርክሾፑ ላይ በደቡብ አፍሪካ ቲሽዋን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር ማሞ ሙጨ ፈጣን ዕድገት ሊያመጡ የሚችሉ አዳዲስ የ PHD ፕሮግራሞችን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መስፋፋት እንዳለባቸው የሚያሳይ ጥናት አቅርበው በጥናቱ ላይ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ልምድ ማግኘት ተችሏል፡፡
በደቡብ አፍሪካ ቲሽዋን ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ ልምዳቸውን ሲያካፍሉ፡፡
በተመሳሳይ የ PHD ፕሮግራም ጥንካሬውን፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ፈተናዎችንና የመፍትሄዎቹን ልምድ በተመለከተ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የድህረ-ምርቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ ቢሻውን ጨምሮ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር አበባው ገበየሁ፣ ዶር በላይ ተሰማና ዶ/ር መሳፍንት ሙጬ የየራሳቸውን የጥናት ተሞክሮ አቅርበው በተመሳሳይ በቤቱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ዉይይት ከተደረገባቸው በኋላ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ በፕሮግራሙ ሃሳቦች በስፋት ተነስተው ውይይት እደተደረገ እና ልምድም እንደተገኘበት ጠቅሰው ወርክሾፑን በመዝጊያ ንግግር ቋጭተዋል፡፡
በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምርቃን ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
ዶ/ር አለማየሁ ቢሻው ጥናታቸውን ሲያቀርቡ፡፡
//ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//

