በጥናትና የምርምር ሥራ ላይ የአቅም ማጎልበቻ ሥለጠና ተሰጠ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሕብረተሰብ ጤና አየባበቅ ትምህርት ክፍል ከታህሳስ 02 እስከ04/2008 ዓ.ም ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ሥልጠናን ለድህረ-ምረቃ ተማሪዎች በሣይንስ አምባ የሥልጠና አዳራሽ ለሦስት ቀናት ያክል መስጠቱን የትምህርት ክፈፍሉ አስተባባሪ አቶ አማረ ታሪኩ ገልጸዋል፡፡
የምርምረና ሕብረተ-ሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታከለ ታደሰ ሥልጠናውን በይፋ ሲከፍቱ እንደተናገሩሩት ለድህረ ምረቃ ተማሪዎች እየተሰጠ ያለው ተግባራዊ የጥናትና ምርምር ሥልጠናው ዓላማ በዋናነት የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ችግር ለመፍታት ያለመ በመሆኑ በዩኒርሲቲያችን የሚቀርቡ የምርምር ሥራዎች በትክክል የማህበረሰቡን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው እና ጥራቱን የጠበቀ የጥናትና ምርምር ሥራም መሰራት እንዳለበት እንዲሁም ከጥናትና ምርምር ሥራው በኋላም በወረቀት ላይ የሰፈረውን ጥናት ወደተግባር በመቀየር የህብረተሰቡን ችግር ልንቀርፍ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ ዶ/ር ሣሙኤል ሳህሌ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው ይህ ተግባራዊ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና በእንስሳት ህክምናና በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ጥናት ለማካሄድ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹ እየሰለጠኑ መማር የሚያስችልቸውና ስልጠናው ቀጣይነት ያለው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የምርምርና ሕብረተሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ታከለ ታደሰ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
በስልጠናው ላይ ተሳታፊ ከነበሩት 30 የድህረ ምረቃ ተማሪዎች መካከል ስልጠናውን አስመልክቶ ያነጋገርናቸው ተማሪ ገዱ ኃይለ ሥላሴ እና ተማሪ ትግስት መኮነን እንደገለጹት የተግባር ስልጠናው የምረቃ ጊዜ ከመድረሱ በፊት ከፍተኛ ልምድ ባላቸው ምሁራን በመሰጠቱ እውቀት ከማግኘታችን ባሻገር የተግባር ሠልጠናው የምርምር ስራዎች ከመጠናቀቃቸው በፊት መሆኑም ለዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራት ከፍተኛ አስተዋጽዖ አለው ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሰለሞን መኮነን የጥናትና ምርምር ስልጠናውን ሲመሩ፡፡
//ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//

