ቪድዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ
የኢትዮጲያ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ፣ የትምህርት ሚኒስተር ድኤታ ዶ/ር ካቫ ኦርጌሳ እንዲሁም ባልደረቦቻቸዉ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአይሲቲ ስማርት ክፍል (Ict smart room) ሚያዚያ 7/2008 ዓ.ም የቀጥታ ቪድዮ ከንፍረንስ አደረጉ፡፡

የኢፈዲሪ ትምህርት ሚኒስተር በሀገሪቱ ያሉትን ከ 33 በላይ የሚሆኑትን ዩኒቨርሲቲዎች በኢንተርኔት መረብ በማገናኘት የትምህርት ስራው ይበልጥ ውጠታማ እንዲሆን እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስማርት ቦርዶችን በመጠቀም ከሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በኢንተርኔት መረብ በመገናኘት እንዴት መማር ማስተማሩን ይበለጥ ማሳደግ እንደሚቻል ፋናወጊ በመሆንና በመተግበር ለትምህርት ሚኒስተር ሃላፊ ለአቶ ሽፈራው ሽጉጤ ና ለደ/ር ከቫ ኦርጌሳ እንዲሁም ለባልደረቦቻቸው በቀጥታ የቪድዮ ስርጭት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የአንዲት ግለሰብ የቀዶ ጥገና ሒደት ምን እንደሚመስል አሳይተዋል፡፡ ቀጥሎም በሆስፒታሉ የታየዉን የቀጥታ ህክምና አስምልክቶ ሚንስትሩ አቶ ሽፈራው ስለፋይዳው ባጭሩ እንዲብራራላቸዉ ጠይቀዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ደ/ር ደሳለኝ መንገሻና የዩኒቭርሲቲዉ የአይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሱራፌል እንግዳዉ የህክምና ተማሪዎች ስለ ቀዶ ጥገና ትምህርት በተግባር ለመከታተል ብዛት ያላቸዉ ተማሪዎች አንድ ክፍል ዉስጥ እንዲገኙ ማድረግ ታካሚውን ለተለያዩ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ ስለሚችል ተማሪወች የሚካሄደዉን ቀዶ ጥገና ባካል መገኘት ሳያስፈልጋቸዉ ስማርት ቦርዶችን በመጠቀም መማሪያ ክፍላቸዉ ላይ ሁነዉ መከታተል ስለሚችሉ ታካሚውን ከስጋት ነጻ ማድረግ እንደሚችል አብራርተዋል፡፡
ፕረዝዳንቱ የቴክኖሎጅዉን ተደራሽነት በማስፋት ሊከሰት የሚችለውን የመምህር እጥረት መፍታት የሚያስችል መሆኑንና በሀገሪቱ ያሉ በተመሳሳይ የትምህርት አይነት የሚገናኙ ተማሪወችን ተመሳሳይ እዉቀት በአንድ ስርጭት እንዲጨብጡ ለማድረግ ስለሚያስችል ጠቀሜታዉ የጎላ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ደሳለኝ ጨምረዉም ዩኒቨርሲቲው በአይሲቲ ክፍል እጅግ በጣም የተደራጀ አሰራር እንዳለና ለወደፊትም አዳዳስ ቴክኖሎጅወችን ለምሳሌ የዩኒቨርሲቲዉን ደህንነት ለመጠበቅ ያስችሉ ዘንድ ከ150 በላይ የዉስጥ ለዉስጥ ካሜራዎችን በመግጠም ላይ እንደሚገኝና መማር ማስተማሩን በማሳለጥ የትምህርት ጥራትንና ተደራሸነትን ለማሳደግ የሚረዱ ሌሎች ዘመናዊና አስፈለጊ ቴክኖሎጅወችን ዩኒቭርሲቲዉ በከፍተኛ ቁርጠኝነት አቅዶ ለመተግበር እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ባጠቃላይ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ደ/ር ደሳለኝ መንገሻና ባልደረቦቻቸው ስለ ስማርት ቦርድ አጠቃላይ ጠቀሜታና ሊደረግላቸው ስለሚገቡ ጥንቃቄዎች ለተከበሩ አቶ ሽፈራው ሽጉጤና ለባልደረቦቻቸው በቀጥታ የቪዮ ኮንፈረንስ ማብራሪያ በመስጠት ዉይይታቸዉን አጠናቀዋል፡፡
ዘጋቢ፡- አምሳሉ ግዛቸዉ

