የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስነ አዕምሮ ትምህርት ክፍል የ2013 ተመራቂ ተማሪዎችን በማስተባበር የሰበሰበውን አልባሳትና ገንዘብ ለካለን ብናካፍል የአረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል ሰኔ 06/2013 ዓ.ም ድጋፍ አደረገ፡፡ የስነ አዕምሮ ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ጎሹ ኔንቆ፣ የትምህርት ክፍሉን የ2013 ተመራቂ ተማሪዎች በማስተባበር የተለያዩ …
በጉባዔው የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የላቀ አስተዋጽኦ ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎች እና የምርምር ተቋማት የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል። ዩኒቨርሲቲያችን ባለፉት 15 ወራት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንደ ሐገር ላበረከተው የላቀ አስተዋጽኦ በክቡር አቶ ደመቀ መኰንን የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚንስትርና የውጭ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት አባላትና ሌሎች ተማሪዎች አገር አቀፍ የተማሪዎች ህብረት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ”Zoom Meeting” ቀጥታ በመቀላቀል ለመሳተፍ የኮኔክሽን መቆራረጥ ችግር ቢያጋጥማቸውም ” ድምፃችን ለነፃነታችንና ለሉዓላዊነታችን” በሚል መሪ ቃል በተዘጋጀው መርሃ ግብር ሰኔ 3/2013 ዓ.ም …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የማርኬቲንግ ትምህርት ክፍል ‹‹የገቢያ ትስስር ለእደ ጥበብ አምራቾች›› በሚል ርዕስ ለጎንደርና አዲስ ዘመን ከተማ የእደ ጥበብ አምራቾች፣ የገቢያና ንግድ ባለሙያዎች ዛሬ ሰኔ 4 እና 5 /2013ዓ/ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንፃ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡ ስልጠናውን …
የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ጋር በመተባበር “Grand Challenge Ethiopia Orentation Workshop for University Researchers”በሚል የሀገሪቱን አበይት የጤና ችግሮች በምርምርና በፈጠራ ለመቅረፍ የሚያስችል አውደጥናት ሰኔ 3/2013 ዓ.ም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሳይንስ አምባ አዳራሽ ተካሄደ። በአውደጥናቱ …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ እንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ ጽሁፍ ትምህርት ክፍል ለአዲስ የፒ ኤች ዲ ተመራቂ ስታፍ አባላት የእንኳን ደስ ያላችሁ ፕሮግራም ሰኔ 03/2013ዓ.ም በማራኪ ግቢ አዘጋጀ። በፕሮግራሙ የዲፓርትመንቱን ኃላፊ አቶ እንደሰው እሸቴን ጨምሮ በርካታ የትምህርት ክፍሉ መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡ትምህርት ክፍሉን የተቀላቀሉ …
የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ሀይል ለማመንጨት በአፍሪካ በአንደኛነት ደረጃ በዓለም አቀፍ ደግሞ በ8ኛ ደረጃ የተቀመጠው የታላቁ የህዳሴ ግድብ በ2015 ዓ.ም ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ግድቡ 6000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል በማመንጨት ከ80% በላይ ለሚሆኑ ኢትዮጵያውያን አሁን ላለባቸው የኤሌክትሪክ ሀይል እጦት መፍትሄ ይሆናል ተብሎ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አዘጋጅነት በማዕከላዊ ጎንደር ፣በምዕራብ ጎንደርና በሰሜን ጎንደር ለሚገኙ የውኃ፣ የመንገድ ፣የኮንስትራክሽ፣የዲዛይን ባለሙያዎች፣አማካሪ ድርጅቶች እና ባለሀብቶች በተገኙበት “Application of Expanded Polystyrene /EPS/Geofoam in Civil Engineering Projects” በሚል ርዕስ ሰኔ 2 እና 3/2013 ዓ.ም በአጼ ፋሲል ግቢ የግንዛቤ …
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ፅ/ቤት አዘጋጅነት ’’ሀገር በቀል የትብብር ፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞች እና አካታች የምርምር ቡድኖች ’’ (Home- Grown Collaborative PhD Programs and 20 New Interdisciplinary Research Groups) በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች ዙሪያ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አስራት …
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት አዲሱን ስትራቴጅክ እቅድ መሰረት ያደረገ የምርምር፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የማህበረሰብ አገልግሎትና የምርምር የትኩረት መስኮች መመሪያ ሰነድ ረቂቅ ግምገማ ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት ሰኔ 01 እና 2 /2013ዓ/ም ተካሂዷል፡፡ በአውደ ጥናቱ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ …


