ሀገራዊ ጉባኤ በጎሃ ሆቴል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጂ አይ ዚ/GIZ ከተሰኘ የጀርመን መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር 5ተኛውን ሀገራዊ የዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉባኤ “የተቀናጀ የዩኒቨርሲቲ፣ ሙያና ቴክኒክ እንዲሁም ኢንዱስትሪ ጥምረት ለሀገር እድገት/Coordinated University –TVET- Industry Coordination for Ethiopia’s Industrialization” በሚል መሪ ቃል ከየካቲት 16 – 17/2010 ዓ.ም በጎሃ ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሂዷል፡፡
የአማራ ክልል ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሰብስበው አጥቃው ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ የጂ አይ ዚ ተወካይ/Higher Education Component Manager, STEP-GIZ ኤቨሊን፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አቶ ብርሀኑ ሙላት፣ ከሁሉም የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ የዘርፉ ሙህራን፣ ከተለያዩ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና የኢንዱስተሪ ተቋማት የመጡ ሙያተኞች በጉባኤው ላይ ተሳትፈዋል፡፡
[widgetkit id=8427]
አቶ ብርሀኑ ሙላት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው “እንደዚህ አይነት ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ ሀገራዊ ጉባኤዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ መዘጋጀታቸው ዩኒቨርሲቲዎችንም ሆነ ሌሎች የቴክኖሎጂ ተቋማትን በተለያዩ መልኩ ተጠቃሚ ስለሚያደርግ ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው” ብለዋል፡፡ አያይዘውም በጂ አይ ዚ አጋርነት የተዘጋጀው ውይይት የተሳካ እንዲሆን ያላቸውን ምኞት ገልጸዋል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝም “ጉባዔው ዩኒቨርሲቲዎች- ከዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም ዩኒቨርሲቲዎች- ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆችና ከኢንዱስትሪ ተቋማት ጋር ያላቸውን ጥምረት ይበልጥ ለማጎልበት ዓለማ አደርጎ የተነሳ ነው፤ በመሆኑም ከዚህ በፊት ያሉ የተለያዩ ችግሮችን ለመቅረፍ እና የተሻሉ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን ለመለዋወጥ ይህ ውይይት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡” በማለት ገልጸዋል፡፡ ተማሪዎች በጽንሰ ሀሳብ ደረጃ የተማሩትን በተግባር ለመፈተሽ የሚያስችለው የኢንተርንሺፕ/Internship ፕሮግራም ውጤታማ ነው ወይ? የሚለውንም ሆነ በኢንዱስትሪዎች ላይ ያአሰራር ስርዓቱ ላይም ሆነ በሰራተኞች ላይ ክፍተቶችና ተያያዥ ችግሮች ካሉ፣ ክፍተቶችንም ሆነ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት መሰል ጉባዔዎች አወንታዊ ሚና እንደሚጫወቱ ዶ/ር ደሳለኝ አያይዘው ገልፀዋል፡፡
በጉባዔው ላይ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ልምድ አካፍለዋል፤ ወጣትና ብዙ ልምድ ያአካበቱ ሙህራንም የምርምር ግኝታቸውንና ጥናታዊ ምርምራቸውን አቅርበዋል፡፡ ለአብነት ያህል፣ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኩል፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ወጣት መምህር አዚዛ ኡመር የፈጠራ ውጤቷን ማለትም ስለ ዲጂታል የማስታወቂያ ሰሌዳ/Digital Notice Board/ አጠቃላይ አጠቃቀም ለተሳታፊዎች ገለጻ አድርጋለች፡፡ በተመሳሳይ አቶ ሰለሞን መስፍን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ዩኒቨርሲቲ – ኢንዱስትሪ ትስስር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ስላሉ የቴክኖሎጅ ሽግግር ስራዎች ለተሳታፊዎች በገለጻ አስረድተዋል፡፡
ያነጋገርናቸው አንዳአንድ ተሳታፊዎች በጉባኤው በነበራቸው ቆይታ በርካታ ልምዶችንና ተሞክሮዎችን እንዳገኙ ገልጸውልናል፡፡ አቶ አያልሰው ዳኘው የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን የርስበርስ ውይይቱ አንዱ ላይ ያለውን አቅም ሌላው እንዲወስድና ኢንዲጠቀም በማድረግ ጉባዔው ምቹ ሁኔታን ፈጥሯል፡፡ ቴክኖሎጅን ለማሸጋገርና ከኢንዱስትሪዎች ጋር ያለው ግንኙነት የላላ በመሆኑ ወደፊት በትኩረት ቢሰራበት ጥሩ ነው ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ብርሀኑ አንተነህ፣ የድሬድዋ ናሽናል ስሜንት ፋብሪካ ከፍተኛ ስልጠና አስተባባሪ፣ ምንም እንኳ በስልጠናው ስሳተፍ የመጀመሪያ ቢሆንም ከዚህ በፊት በዩኒቨርሲቲና በኢንዱስትሪ መካከል ያለውን ክፍተት ለመሙላት ያስቻለ ውይይት ነብር ብለዋል፤ አያይዘውም ለበለጠ ውጤታማነት የተነሱ ሀሳቦችን መሬት ላይ ማውረድ ይገባልም ብለዋል፡፡
ዘገባ፡ አምሳሉ ግዛቸው
የህዝብና ዓለምዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

