ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የአካባቢ እና ተፈጥሮ-ሃብት ኢኮኖሚክስ ትምህርት ክፍል (Environmental and Natural Resource Economics Department ) በጎንደር ዩኒቨርስቲ፣ በኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት (School of Economics) ስር ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ በመደበኛ (Regular) እና ተከታታይ (Extension) መርሃ-ግብር የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ቆይቷል፡፡ በመሆኑም ያለውን የሰው ሃይልና የመቀበል አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት በ2010 ዓ.ም በሁለተኛው ወሰነ-ትምህርት በተከታታይ (Extension) መርሃ-ግብር የሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተምር ይፈልጋል፡፡
የዲግሪ ስያሜ፡ (Master of Science in Economics (Major in Environmental and Natural Resource Economics)
የመመዝገቢያ ጊዜ፡ ከ 29/05/2010 እስከ 12/06/2010 ዓ.ም፡፡
የመመዝገቢያ ቦታ፡
1. የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ረዳት ሬጅስትራል ጽ/ቤት ወይም
2. የኢኮኖሚክስ ትምህርት ቤት በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ህንጻ 5ኛ ፎቅ፡፡
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን 18/06/2010 ዓ.ም መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Call for Application
Master of Science in Economics

