ለአዲስ ትምህርት ፈላጊዎችና ለነባር የክረምት ተማሪዎች በሙሉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2008 ዓ.ም በክረምት መርሃ ግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡ የስልጠና መስኮች
|
|
የመግቢያ መስፈርት
በትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ፤ ይኸውም
1) በመምህርነት ሙያ ለመሰልጠን የሚያመለክቱ በ 10+3 ወይም 12+2ደረጃ በዲፕሎማ የተመረቁና በሙያው በማገልገል ላይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ወይም;
2) ከቴክኒክና ሙያ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ለሚገቡ በ10+3 ወይም 12+2 ደረጃ በዲፕሎማ የተመረቁ፤ ቢያንስ የደረጃ 4 የሙያ ብቃት ምዘና ወስደዉ ብቁ የሆኑ፤ የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ተፈትነዉ ያለፉ እና በሙያው በማገልገል ላይ ስለመሆናቸው ማስረጃ የሚያቀርቡ ወይም;
3) የመሰናዶ ፕሮግራም አጠናቀዉ የዘመኑን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ዝቅተኛ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ በመሰናዶ ፕሮግራም በነበሩበት የትምህርት መስክ (social Science/Natural Science) በፈለጉት የትምህርት ዓይነት መማር ይችላሉ ወይም;
4) በአንድ የትምህርት መስክ የመጀመሪያ ዲግሪ ኖራቸዉ በሌላ የትምህርት መስክ የዲግሪ ፕሮግራም መማር የሚፈልጉ አመልካቾች በሚፈልጉት የማህበራዊ ሳይንስ ወይም ተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተመዝግበው መማር እንዲችሉ ወይም;
5) ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በዲፕሎማ የተመረቁ አመልካቾች የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደዉ ካለፉ በተመሳሳይ የትምህርት መስክ የዲግሪ ፕሮግራም መቀጠል እንዲችሉ፤
ምዝገባ፡-
የምዝገባ ቀን፡- ለአዲስ ተመዝጋቢዎች ከ18/09/ 2008 ዓ.ም እስከ 15/10/ 2008 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓትና ቀን መመዝገብ ይችላሉ፡፡ ለነባር የክረምት ተማሪዎች ከሰኔ 30/ 2008 ዓ.ም እስከ ሃምሌ 01/2008 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ ይኖርበወታል፡፡
የምዝገባ ቦታ፡- በየኮሌጅ፤ ፋካሊቲ ወይም ትምህርት ቤት ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤት፤
ማሳሰቢያ ፡-
· አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የ10ኛ፤ 12ኛ ክፍል የፈተና ዉጤና ትራንስክሪፕት እና ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ ይዘዉ መቅረብ አለበወት፤ እንዲሁም ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለጎንደር ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር በፖ.ሳ.ቁ 196 ማስላክና የከፈሉበትን ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርበወታል፡፡
· በመንግስት እስፖሰርነት የሚማሩ ትምህርቱን ከፈቀደላቸው መ/ቤት ድብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 58 211 2639 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የተከታታይ ትምህርት ፕሮግራሞች ዳይሬክቶሬት

