ላይ የማንቃቂያ ፕሮግራም ተካሄደ
የCapacity Building and mentorship Partnership (CBMP) Project የጤና መረጃ አያያዝን በተመለከተ ከኢንፎርማቲክስ ፋካልቲ፣ ከቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት እና ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለተውጣጡ 24 ባለሙያዎች ከሚያዚያ 3 – 6/2010 ዓ.ም ድረስ የቆየ ስልጠና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ በተመረጡ ወረዳዎች ሥራውን ለመጀመርና የተሰጠውን ሥልጠና ወደተግባር ለመቀየር የማነቃቂያ ፕሮግራም አስፈላጊ በመሆኑ ሚያዝያ 09/8/2010 በታዬ በላይ ሆቴል ውይይት ተካሂዷል፡፡ በውይይቱ የጎንደር ዩኒቭርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ደሳለኝን መንገሻን ጨምሮ የፌደራል ጤናጥበቃ ሚኒስተር፣ የአማራ ክልልና የቤንሻንጉል ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ፣ የሰሜን ጎንደር ዞን ጤና መምሪያና የተለያዩ ዩኒቭሲርቲዎች ተወካዮች፣የዩኒቭርሲቲያችን ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖችና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል፡፡
[widgetkit id=8928]
በፕሮግራሙ የጎንደር ዩኒቭርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ በንግግራቸው እንደገለጹት የጤና መረጃ አያያዝ ልምዳችን ወደኋላ የቀረ መሆኑን ጠቅሰው የጎንደር ዩኒቭርሲቲ ሆስፒታል መረጃ አያያዝ ለመስተካከል ከፍተኛ ድካም ሚጠይቅ ቢሆንም የተመረጡን ወረዳዎችን ጨምሮ ከጤና ሚኒስተር ጋር በመተባበር ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን እንዲከተሉ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የሃሳቡ አመንጭ የሆኑትን ዶ/ር ቢኒያም ጥላሁን የሄልዝ ኢንፎርማቲክስ ትምህርት ክፍል ኃላፊና የፕሮጅክቱ አስተባባሪን በማመስገን እና ኃላፊነቱ የዚሁ ክፍል ብቻ እንዳይሆን በሥልጠናው የተሳተፉት ክፍሎች ጭምር ትኩረት ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
ዶ/ር ቢኒያም የፕሮጅክቱን ዓላማ በተመለከተ በዝርዝር ካቀረቡ በኋላ ሃሳቦች እየተነሱ ከፍተኛ ውይይት ተካሂዷል፡፡ ዘመናዊ የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማስፋፋት የተመረጡ ወረዳዎችን በሞዴልነት በመያዝ ወደ ሌሎች ተቋማት መሻጋገር እንዳለበት በውይይቱ ሃሳቦች ተነስተውና መልስ ተሰጥቶባቸው ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
የሕ/ዓ/አ/ግ/ዳይሬክቶሬት

