ማስታወቂያ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በየዓመቱ ከሚያከናዉናቸዉ ዋናዋና ተግባራት መካከል አንዱ የሆነዉ አመታዊ የትምህርት ጥራት ጉባኤ መጋቢት 7 እና 8፤ 2010 ዓ.ም ለ5ኛ ጊዜ ይካሄዳል፡፡ ሁለት ቀን በሚቆየዉ በዚህ ዝግጅት ላይ በመጀመሪያዉ ቀን የትምህርት ሚኒስትሩን ጨምሮ ከተለያዩ ተቋማት የተጋበዙ እንግዶች የሚገኙ ሲሆን ፤ በትምህርት ጥራት ዙሪያ የተሰሩ የጥናትና ምርምር ዉጤቶች ቀርበዉ ዉይይት ይደረግባቸዋል፡፡
በሁለተኛዉ ቀን ሁሉም ኮሌጆች/ፋኩሊቲዎች/ኢንስቲቲዉቶች/ት/ት ቤቶች በየራሳቸዉ የትምህርት ጥራት ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፣ የኦዲት ዉጤቶች ይቀርባሉ፣የተማሪዎች አጠቃላይ የመዉጫ ፈተናን በሚመለከት እና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ሁሉም መምህራን በቀጥታ በሚሳተፉበት መልኩ ዉይይት ይደረጋል፡፡በመጨረሻም በማጠቃለያ ዉይይት እና በመዝጊያ ንግግሮች የሚጠቃለል ይሆናል፡፡
በነዚህ ቀናት መደበኛ የትምህርት ክፍለ ጊዜዎች እንደማይኖሩ ታዉቆ ሁሉም መምህራን በመሳተፍ ለትምህርት ጥረት መሻሻል የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግ እናሳስባለን፡፡
የትምህርት ጥራት ዳይሬክቶሬት

