ራዕይ
2027 ዓ.ም. በዓለም አቀፍ ደረጃ የታወቀ የአማራ ምድርና የአማራ ሕዝብ የስልጠናና ምርምር የልህቀት ማዕከል ሆኖ ማየት
ተልዕኮ
የአማራ ህዝብ ባህልን፣ ትውፊትን፣ ታሪክን፣ ኪነ-ጥበብን፣ የስነ-ልቦና ስሪትን፣ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ሃብቶችን፣ ሳይንሳዊ አበርክቶዎችን ለመመርመርና ለማጥናት፣ ለመጠቀምና ሰንዶ ለማቆየት እንዲቻል ግንዛቤ መፍጠር፣ ብቁ ባለሙያዎችን ማሰልጠንና ማፍራት የተቋሙ አንዱ ተልዕኮ ነው፡፡ ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ለተመራማሪዎች፣ ለሙሁራን እና ለባለሙያዎች ትብብር የሚያደርጉበት እና ሃሳባቸውን በነፃነት እንዲለዋወጡ የሚያስችል መድረክ ሁኖ እንዲያገለግል ማድረግም ሌላው ተልዕኮ ነው፡፡
ዓላማ
አጠቃላይ ዓላማ
የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን በተደራጀ ሁኔታ ማጥናት፣ መመርመር፣ መሰነድና ለጥቅም ማዋል
ዝርዝር ዓላማዎች
• የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን ላይ ትኩረት ያደረጉ የትምህርት ፕሮግራሞችን መቅረፅና መስጠት፤
• የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን ላይ ጥናትና ምርምር ማድረግ፤
• የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን ላይ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን በትምህርታዊ መጽሔቶች ላይ ማሳተም፤
• የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን ላይ የሚደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶችን የሚታተሙበት መጽሔት ማቋቋም፤
• ከአማራ ምድርና ህዝብ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን የመጻሕፍት፣ የብራና ጽሑፎች እና ሌሎች ሰነዶችንና የህትመት ውጤቶችን የሚይዝ አካታች ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት

