ስለ አዕምሮ ጤና ስልጠና ተሰጠ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ስለ አዕምሮ ጤና ለደንቢያ ወረዳ ለ25 የቀበሌ ሊቀመናብርተና እና ለ25 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በቆላድባ ከተማ ከግንቦት 15-28/2008 ዓ.ም ስልጠና ሰጠ፡፡

ረዳት ፕሮፌሰር ብሃኑ ቦሮ ስልጠና ሲሰጡ
ስልጠናዉ ለሊቀመናብርት ከግንቦት 15-19/2008 ዓ.ም ለአምስት ቀናት እና ለጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ከግንቦት 19-28/2008 ዓ.ም ለ10 ቀናት ስለ አዕምሮ ጤና ምንነት፣ የአዕምሮ ህመም አይነቶች እና መንስኤዎቻቸዉ እንዲሁም ስለአዕምሮ ህመም ህክምና ስልጠና ተሰጠ፡፡

ሰዎች የአዕምሮ በሽተኛ ሆነዉ እንደማይወለዱ፤ ከተወለዱ በኋላ ማንኛዉም ሰዉ በተለያዩ ምክንያቶች በሕይወት ዘመናቸዉ የአዕምሮ ህመም ሊይዛቸዉ እንደሚችል ነገር ግን በወቅቱና በጊዜዉ ከታከሙ ብዙዎቹን የአዕምሮ ህመሞች ማከም እንደሚቻል አሰልጣኝ መምህራን ረዳት ፕሮፊሰር ብርሃኑ ቦሮ እና መ/ር ወንዳለ ጌትነት ለሰልጣኞች ተናግረዋል፡፡
አሰልጣኝ መምህራን እንዳሉት በተለያዩ አካባቢዎች ጥቂት የማይባሉ አዕምሮ ህመም ያለባቸዉ ሰዎች እንደሚገኙና ዘመዶቻቸዉ በወቅቱ ወደ ህክምና እንደማይወስዷቸዉ በምትኩ ህክምና ወደ ማያገኙበት ቦታ እንደሚወስዷቸዉ በመጨረሻም ህምሙ ሳይሻላቸዉ ሲቀር እጅና እግራቸዉን አስረዉ እንደሚያስቀምጧቸዉ ገልጸዋል፡፡ ይህ ተግባር ተገቢነት እንደሌለዉና የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ከቀበሌ ሊቀመናብርት ጋር በጋራ ሊሰሩና ሊያስተምሩ እንደሚገባ ትምህርት ሰጠዋል፡፡
አንዳንድ ሰልጣኞች እንዳሉት ስልጠናዉ እነስከተሰጣቸዉ ድረስ በአዕምሮ ጤና ላይ ስራዎችን እነዳልሰሩ ገለጸዉ ወደ ፊት ግን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሰጣቸዉ ስለጠና መሰረት በሚሰሩበት አካባቢ ማህበረሰቡን እንደሚያስተሩ ገልጸዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ደምሴ ደስታ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

