በድጋሚ የነባርና አዲስ ተማሪዎች የቅበላ ጊዜ ማስተካከያ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ነባርና አዲስ ተማሪዎችን የምንቀበልበትን ጊዜ በፌስቡክና በዌብሳይት ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡ ቢሆንም የቅበላ ጊዜው ላልተወሰነ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን እናሳስባለን፡፡ ወደፊት አዲስና ነባር ተማሪዎችን የምንቀበልበትን ጊዜ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የምንገልፅ ይሆናል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

