በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልዩ የሆነ ስነ-ጥበባዊ ዝግጅት ተካሄደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የባህል ኪነ-ጥበብ ማዕከል ጥር 18/2008 ዓ.ም በሰይንስ አምባ የስብሰባ አዳራሽ ልዩ የሆነ ስነ-ጥበባዊ ዝግጅት ተካሂዷል፡፡ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ የሊቁ አለቃ ገብረሃና መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ ያላቸውን ዕውቀት መጠቀም እንዲችሉ እና ከታዋቂ አርቲስቶች ልምድ እንዲቀስሙ ለማስቻል ነው፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳነት ዶ/ር ደሳለኛመንገሻ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
ውይቱን በንግግር የከፈቱት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ ዩኒቨርሲቲያችን በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ታዋቂ አርቲስቶችን በመጋበዝ ተማሪዎቻችን ልምድ እንዲቀስሙ ማድረግ ችለናል፣ይህምሁኔታ ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም በዕለቱ በእንግድነት ከተጋበዙት ታዋቂ አርሲቲስቶች መካከል አርቲስት ንብረት ገላውና አርቲስት ደሳለኝ ኃይሉ የዩኒቨርሲቲውን ጥሪ አክብረው በመገኘታቸው ዶ/ር ደሳለኝ ምስጋና ከሰጡ በኋላ ተማሪዎችም የአርቲስቶቹን ተሞክሮ በመውሰድ በኪነ-ጥበቡ ዘርፍ የራሳቸውን አስተዋፆ እንዲያበረክቱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

አርቲስት ንብረት ገላው በጎንደርዩኒቨርሲቲ ተገኝተው ለምዳቸውን ለተማሪዎች ሲያካፍሉ፡፡
በዝግጅቱ መስማት የተሳናቸው በጎንደር ከተማ የጻዲቁ ዩሃንስ ትም/ት ቤት ተማሪዎች ድራማ አቅርበዋል፡፡ አርቲስት ንብረት ገላውም መስማት ለተሳናቸው ተማዎች አድናቆታቸውን ገልፀው ወደፊት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲና ከጎንደር ከተማ አስተዳደር ጋር በመሆን መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች ልዩ የሆነ ት/ቤት እንገነባለን ሲሉ ያላቸውን ስነ-ጥበባዊ ድጋፍ ገልፀዋል፡፡

ከግራ ወደቀኝ አርቲስት ገላው እንየው፣ከመካከል የጎንደርዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ እና በግራ በኩል የአስተዳደር ም/ፕሬዚዳንት አቶ ሰለሞን አብርሃ በዝግጅቱ ላይ ፡፡

ከግራወደቀኝ አርቲስት ደሳለኝ ሃይሉ፣ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ፣ፕ/ማሞ ሙጬ፣አርቲስት ንብረት ገላው፣ አቶ ሙሉቀን ዘመነና አቶ ሰሎሞን አብርሃ በባህልና ኪነጥበብ ምሽቱ በተገኙበት ሰዓት፡፡
//ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//

