በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በስነ ትምህርት ፋኩልቲ ዓለም አቀፍ ወርክሾፕ እየተካሄደ ነው፡፡
በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች የአካቶ ትምህርት በሚመለከት በሚካሄደው ወርክ ሾፕ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር መርሻ ጫኔ፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ ከኦስትሪያ ቬና ዩኒቨርሲቲ እና ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመጡ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል መምህራንና የ
በኦስትሪያ የልማት ፕሮግራም ፈንድ ከሚደረገው የ‹APPEAR› ፕሮጀክት ውስጥ አንዱ የሆነው
[widgetkit id=8908]
ፕሮጀክቱ በዩኒቨርሲቲዎቹ በመማር ላይ ያሉ ተማሪዎችን አቅም የሚያጎለብቱ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት ሚያዚያ 09/ 2010 ዓ.ም በሩት ሆቴል በተካሄደው ወርክ ሾፕ ዩኒቨርሲቲዎቹ በአንድ አመት ቆይታቸው ያከናወኗቸውን ተግባራት አቅርበዋል፡፡ ፆታንና አካል ጉዳትን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች በሚመለከት በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ላይ ጥናት መካሄዱ፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን አቅም ሊያጎለብቱ የሚችሉ የተለያዩ ስልጠናዎች መሰጠታቸው፣ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ሊጠቀሙባቸው የሚችሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ግዥ መፈፀሙ እንዲሁም የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ያላቸውን መስተጋብር ለማጠናከር የሚሰሩ ስራዎች በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸውን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የስነ ትምህርት ፋኩልቲ ዲን እና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ APEAR ፕሮጀክት አስተባባሪ የሆኑት ወ/ሮ መሰረት ሀሰን ገልፀዋል፡፡
ሚያዚያ 10/2010 ዓ.ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም ህንፃ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡ የፓናል ውይይቱን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የከፈቱት ሲሆን፣ ዩኒቨርሲቲው ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች እየሰራ ያለውን የመሰረተ ልማት ስራዎችና ሌሎች ተግባራት ገልፀው ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈሪ እና ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ ያላቸውን እውቀት እና ልምድ ለማካፈል ወደ ኒቨርሲያችን በመምጣታቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ “አካል ጉዳተኝነትና ማህበራዊ መስተጋብር በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት” በሚል ርዕስ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት የዓለም ሎሬት ሊቃነ ምሁራን ፕሮፌሰር ጥሩሰው ተፈሪ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል፡፡ በፅሁፋቸው በአካል ጉዳተኞች ዙሪያ ስላሉ ዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች፣ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች በልዩ ትምህርት ቤቶች እና በመደበኛ ትምህርት ቤቶች እንዴት እየተቃኙ ነው? የሚለውን እንዲሁም አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ከጨረሱና ከተመረቁ በኃላ ስራ ለመቀጠር በሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በመጨረሻም ለችግሮቹ መፍትሄ ያሏቸውን ነጥቦች በመጠቆም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አሳይተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የብርሀን ለዓለም አለማቀፍ አማካሪ እና የህግ ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ የትነበርሽ ንጉሴ የአካል ጉዳተኛ ተማሪዎችን የሚያነቃቁ እና ለውይይት መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦችን አቅርበዋል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የፖሊሲ ለውጥ ለማምጣት ትልቅ አቅም በመሆናቸው በአካቶ ትምህርት እና በልዩ ፍላጎት ትምህርት ዙሪያ ጥናቶች ሊደረጉ ይገባል ብለዋል፡፡ወ/ሮ የትነበርሽ አክለውም ለአካል ጉዳተና ተማሪዎች ማህበራዊ መስተጋብር ማደግ ጥናቶችን ከማድረግ በተቸማሪ ተከታታይ የሆኑ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎች ያስፈልጋሉ ብለዋል፡፡ በመወያያ መነሻ ሀሳቦች ላይም ውይይት እተካሄደ ነው፡፡
ወርክ ሾፑ እስከ ሚያዚያ 12/2010 ዓ.ም የሚቀጥል ሲሆን፣ በመርሀ ግብሩ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ስነ ትምህርት ፋኩልቲ ልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት ትምህርት ክፍል

