በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የዓለም ኤድስ ቀን ተከበረ
በኢትዮጵያ የህክምና ተማሪዎች ማህበር ጎንደር ቅርንጫፍ በዓለም ለ12ኛ፣በሃገራችን ለ11ኛና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለ7ኛ ጊዜ የሚከበረውን የዓለም ኤድስ ቀንን ታህሳስ 02/2008 በአጼ ቴወድሮስ ግቢ ውስጥ ፣‹‹Gtting to zero››/ኤችአይቪ ኤድስን ዜሮ ማድረስ/ በሚል መሪቃል አክብሮ ውሏል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ በበዓሉ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡-በኤችአይቪ ኤድስ ለተያዙና ለተጎዱ ወገኖቻችን ድጋፍና ክትትል ለማድረግ፣ከኤችአይቪ ኤድስ ነፃ የሆነ ትውልድ ለመፍጠርና በጋራ ለመስራት ቃል የምንገባበት ዕለት ነው በማለት ገለልጸዋል፡፡ በተጨማሪም በበሽታው ምክንያት ህይወታቸውን ያጡ ወገኖቻችንን የምናስብበት መልካም አጋጣሚ ነው ካሉ በኋላ ኤችአይቪ ኤድስን ለመከላከል የሚደረጉ የበጎአድራጎት እንቅስቃሴዎችን ዩኒቨርሲቲው የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
የ3ኛና የ5ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች ተማሪ ጌታቸው አማረ የማህበሩ ፕሬዚዳንት፣ ተማሪ ዮርዳኖስ ግርማ የማህበሩ ም/ፕሬዚዳንትና ተማሪ ታሪኩ ሁሴን የበዓሉ ዝግጅት አስተባባሪ የማህበሩን ዓላማና ማህበሩ እያከናወናቸው ያለውን የበጎ አድራት እንቅስቃሴዎችን አስመልክቶ እንደገለጹት የሥነ-ተዋልዶና ኤችአይቪ ኤድስ፣የበጎ አድራጎት፣ዩኒቨርሲቲውን ከሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የማገናኘት፣የሕብረተ-ሰቡን ችግር መፍታት፣በሕክምናና ጤና ሣይንስ ኮሌጅ የተማሪዎችን ጥያቄ መፍታትና ተማሪዎችን ማዝናናት የሚሉ 6 ዓላማዎች እዳሉትና ከ260 በላይ አባላትን ይዞ በመንቀሳቀስና ከደም ባንክ ጋር በመተባበር ከ600 ዩኒት በላይ ከታማሪዎች የደም ለገሳ የተደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ማህበሩ የበዓሉን ፕሮግራም ሲያዘጋጅ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ በተገኘ የ90 ሺህ ብር ድጋፍ ሲሆን በዓሉን ሊገልጹ የሚችሉ ከ500 በላይ ቲሸርቶች፣ከ800 በላይ ብሮሸሮችና ከ5 ያላነሱ ባነሮች ተዘጋጅተው ለበዓሉ ድምቀት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡በተጨማሪም በዓሉን አሰመልክቶ የሥዕል ኢግዚቪሽንና ውድድር፣የፓናል ውይይትና የእግር ኳስ ውድድር ተካሂዶ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ የመዝጊያ ንግግር ካደረጉ በኃላ የበዓሉ ፍጻሜ ሁኗል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ በበዓሉ የፎቶ ኢግዚቪሺንና ውድድርሩን ሲጎበኙ፡፡

የተማሪዎችዲን አቶ አንተነህ ደመቀና ተማሪ ጌታቸው አማረ የማሕበሩ ፕሬዚዳንት ማሕበሩን በተመለከተ ንግግር ሲያደርጉ፡፡
//ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት/

