አለም ዓቀፍ የፊስቱላ በዓል ተከበረ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአለም ዓቀፍ ደረጃ ለ3ኛ ጊዜ የሚከበረዉን የፊስቱላ ቀን “ፊስቱላ በእኛ ትዉልድ ይብቃ” በሚል መሪ ቃል መንግስታዊና መንግስታዊና ካለሆኑ ድርጅቶች የመጡ ሀላፊዎችና ተወካዮች በተገኙበት በጎንደር ሪፈራል ሆሰፒታል ግንቦት 15/2008 ዓ.ም በተለያዩ ዘግጅቶች ተከበረ፡፡

ዶ/ር ሲሳይ ይፍሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የመክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ
በዚህ ደማቅ በዓል ላይ የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ተወካይ፣ የክልሉ ጤና ቢሮ ተወካይ፣ የUNFPA ተወካይ፣ የዞን ጤና መምሪያ ሃላፊ እና የተለያዩ ተጋብዠ እንግዶች በበአሉ ተገኝተዋል፡፡
በእለቱ ጥናታዊ ጽሑፎች በዶ/ር ሙላት አደፍርስ፣ በዶ/ር ኪሮስ ተረፈ እና የፌደራል ጤና ጥበቃ ሚኒስተር ተዋካይ በሆኑት በሲስተር ነፃነት በለጠ እንዲሁም ባለፉት አምስት አመታት የተሰሩ ስራዎችንና ያጋጠሙ ችግሮች በአቶ አዝመራዉ አድጎ ቀርበዋል፡፡ በቀረቡት ጽሑፎች ላይ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡

አቶ አዘመራዉ አድጎ የፊስቱላ ፕሮጀክት መአከል አሰተባባሪ በአለፉት አምስት አመታት የተሰሩ ስራዎችን ሲያቀርቡ
አቶ አዝመራዉ አድጎ ባቀረቡት ጽሑፋቸዉ እንደገለጹት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አለምቀፍ የፊስቱላ ስለጠና ማዕከል ህክምና መስጠት የጀመረዉ Women’s and Health Aliance International (WAHA) ከተባለ ግበረ ሰናይ ድርጀት ጋር በመተባበር በ2001 ዓ.ም እንደሆነና በወቀቱ በሰባት አልጋዎች በጽንስና ማህጸን ክፍል እስከ 2002 ዓ.ም ለአንድ አመት ያክል ህክምናዉን ሲሰጥ አንደቆየ ተናግረዋል፡፡ የጎንደር ዩኒቭርሲቲ የጀመረዉን ህንጻ WAHA በማጠናቀቅ፣ ከUNFPA በእዳታ በተገኘ 70 የህሙማን አልጋ እና የህክምና መስጫ መሳሪያዎች ሐምሌ 2003 ዓ.ም በተጠናከረ መልኩ እንደ አዲስ ስራዉን እንደጀመረ አስታዉሰዋል፡፡ የፊስቱላ ስልጠናና ህክምና ማዕከል ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ከሰሜን እና ከደቡብ ጎንደር ዞኖች የተለያዩ ወረዳዎች ከምስራቅና ከምዕራብ ጎጃም ዞኖች ለመጡ 945 ለሚሆኑ በፊስቱላ በሽታ ሲሰቃዩ ለነበሩ እናቶች ነፃ ህክምና እንዲያገኙ እንዳደረገ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የፊስቱላ ማዕከል አስተባባሪ አቶ አዝመራዉ አድጎ ተናግረዋል፡፡
አቶ አዝመራዉ አድጎ አያይዘዉም ማዕከሉ ከUNFPA እና Integrated Family Health Program (IFHP) ጋር በመተባበር ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል አለምቀፍ የፊስቱላ ስልጠና ማዕከል የሚመጡ ህሙማንን የትራንስፖርት እና ሌሎች ተያያዥ ወጭዎችን በመሸፍን ህሙማን ወደ ማዕከሉ መጥተዉ ህክምና እንዲያገኙ እየተደረገ ቢሆንም የትራነስፖርት ችግሩን መቀረፍ እንዳልተቻለ እና ችግሩ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የመጡ ሁለት አናቶች የፊስቱላ በሽታን በተመለከተ ተሞክሯቸዉን እና የሰሯቸዉን መልካም ተግባራት ለበአሉ ታዳሚ አካፍለዋል፡፡በመጨረሻም ሰላማዊ ሰልፍ በመስቀል አደባባይ በማካሄድ ባዓሉ ተፈጽሟል፡፡
ዘጋቢ፡ ይላቅ አለባቸዉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ከፍተኛ ሪፖርተር
አርታኢ፡ ኤሊያስ መንበረ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ቡድን መሪ

