አካባቢን ለሥራ ምቹ ማድረግ የተገልጋይነት እርካታን ይጨምራል
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በውስጡ አምስት ግቢዎች ያሉት ሲሆን አካባቢን ውብ፣ ጽዱና ማራኪ ማድረግ በሚል አጀንዳ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ ግቢዎቹን የማስዋብ ሥራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህን መልካም ጅማሮ የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል መጋቢት 2/2010 ዓ.ም በህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና በሪፈራል ሆስፒታሉ ሁለት ዓላማዎች ያሉት የፅዳት ዘመቻዎች ተካሂዷል፡፡
አንደኛው አካባቢን ውብ፣ፅዱና ምቹ ማድረግ ከአንድ ጤና ተቋም የሚጠበቅ ዘመናዊነት ነው የሚል ሲሆን ሌላኛው ደግሞ በጤናው ዘርፍ የትራንስፎርሜሽኑ አጀንዳ እንደሚያስቀምጠው ርህሩህ፣ አክባሪና ተንከባካቢ የጤና ባለሙያና ተገልጋይ መፍጠር የሚል ነው፡፡
[widgetkit id=8367]
የፅዳት ዘመቻውን አስመልክቶ የህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና የሪፈራል ሆስፒታሉ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሲሳይ ይፍሩ እንደገለጹት የፅዳት ዘመቻው /አካባቢን ማፅዳት/ የአንድ ተቋም ኃላፊነት ብቻ ሳይሆን ወደሌሎች ተቋማትና ማህበረሰብ ሊሸጋገር የሚገባው ተግባር በመሆኑ ግቢያችንን ለሥራ ምቹ በማድረግ ወደሌሎቹ እንዲሸጋገር ጥረት እናደርጋለን በማለት ብለዋል፡፡ በዕለቱ በፅዳት ዘመቻው ተሳታፊ የሆኑት መምህራን፣ተማሪዎች፣የአስተዳደር ሰራተኞችና ኃላፊዎች የበለጠ እንዲጠናከሩ በቀጣይ በየሦስት ወሩ አንድ ጊዜ አካባቢን የማፅዳት ፕሮግራም ዕቅድ ተይዞ እንቅስቃሴ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በፅዳት ዘመቻው ከተሳተፉት ባለሙያዎች መካከል የህ/ጤ/ሳ/ኮ/እና የሪፈራል ሆስፒታሉ በሰው ሀብት ማሰተባበሪያ ጽ/ቤት የዕቅድና ጥናት በለሙያ የሆኑት አቶ ማንአየ ባዩህ እንደገለጹት የጤናው ተቋም ማህበረሰብ ተነሳሽነቱን ከሚያሳይበት አንዱ መንገድ በመሆኑ የግቢያችንን ውበት ለመጠበቅ በትጋት እንሰራለን በማለት ቃል ገብተዋል፡፡ አካባቢን ውብና ጽዱ ማድረጉ ለሰራተኛውና ለተገልጋዩ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ወደፊት ተከታታይ ፕሮግራም ወጥቶለት ወደሌሎች ተቋማትና ማህበረሰብ ጭምር እንዲሸጋገር መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ዘጋቢ፡- በላይ መስፍን
ሕ/ዓ/አ/ግ/ዳይሬክቶሬት

