ኤምሬትስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ የአመራርነት ስልጠና ሰጠ እንዲሁም ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ
መሪነት ስልታዊነትን፣ ምክንያታዊነትንና የሰዎችን ችግር መረዳትን የሚጠይቅ ኃላፊነት ነው፡፡ ሁሉም ሰው የመሪነት ጥበብ ተችሮት አይወለድም፤በእድሜ፣ በልምድና በትምህርት ያዳብረዋል እንጂ፡፡
ይህን ታሳቢ በማድረግም ከሱዳን ኤምሬትስ ኮሌጅ የመጡት ሀሰን ሙሀመድ ኢብራሂም ከሰዎች ጋር የመግባባት ጥበብ በሚል ርዕሰ ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአመራር ስታፍ አባላት ስልጠና ሰጥተዋል፡፡ ስልጠናው በሰዎች የመግባባት ሂደት ላይ መልካም የሚባሉ እና የማይመከሩ ባህርያትን በግልጽ ያሳየ ነበር፡፡
[widgetkit id=8787]
በዚህ የኢንፎርማቲክስ ፋኩልቲ በአዘጋጀው ስልጠና አካዳሚክ ም/ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ በርካታ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡ የሱዳኑን ኤምሬትስ ኮሌጅ ወክሎ የመጣው ልዑካን ቡድን የኮሌጁ ዲን ፕ/ር ሳይፍ ኤልድን ፋቶህን፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር ባቢከር ማህጁብ ሙሳን፣ የውጭ ጉዳይ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሀሰን ሙሀመድ ኢብራሂምን እና ሌሎችንም ያካተተ ነበር፡፡ ስለሆነም የልዑካን ቡድኑ አባላት ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር በትስስር ለመስራት ያላቸውን ፍላጎት አሳይተዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ኤምሬትስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የሚያተኩረው በሰራተኞችና ተማሪዎች ልምድ ልውውጥ፣ በምርምር ስራዎችና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ እንደሆነ በስምምነቱ ወቅት ተገልጧል፡፡ ሁለቱን ተቋማት በመወከል ሰነዱን የተፈራረሙት ዶ/ር አስራት አጸደወይንና ፕ/ር ሳይፍ ኤልድን ፋቶህ በቀጣይ ሁለቱም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በትስስር እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል፡፡
በደስታው ዋኘው
የህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

