ማቋቋም፤
• የአማራን ምድርና ህዝብ ማህበራዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና ተፈጥሯዊ ጉዳዮችን ላይ የማማከር አገልግሎት መስጠት፤
• አማርኛን የሳይንስ ቋንቋ ማድረግ
• የአገራችንን የተለያዩ ቋንቋዎች በኢትዮፒክ ስክሪፕት (በአማርኛ ፊደላት) ማስተማርና ስልጠና መስጠት፤
የተቋሙ እሴቶች
• ልህቀት፡- ተቋሙ በሁሉም ተግባራቱና እንቅስቃሴው የላቀ ሙያዊ እሴትን የጠበቀ ይሆናል፡፡
• ከወገንተኝ ነፃ፡- ተቋሙ ከርዕዮተ ዓለም፣ ከሐይማኖት፣ ከፖለቲካ እና ከሌሎች ጉዳዮች ወገንተኝነት ነፃ ነው፡፡
• ፋይዳ፡- ተቋሙ የአማራ ህዝብ ጉዳይ ላይ ለሚነሱ አርዕስቶች የአጭርና የረጅም ጊዜ ለፖሊሲ ቀረጻና ለሌሎች ፍላጎቶች ግብዓት የሚሆኑ ጠቃሚና ተገቢ ሃሳቦችን በማቅረብ ፋይዳ ያለው ተቋም ይሆናል፡፡
• ራስ ገዝነት፡- ተቋሙ ከማህበረሰቡ እና ከተለያዩ ድርጅቶች የሚያገኘውን የተለያዩ ድጋፎች እንዳሉ ሁነው ከየትኛውም ዓይነት ፖለቲካዊና አስተዳዳራዊ ተዕፅኖ ነፃ ሁኖ ዓላማዎቹን ያሳካል፡፡
• አገራዊነትና ዓለም አቀፋዊነት፡- ተቋሙ የአገራችንና የዓለም አቀፍ ሙሁራንን ያቀፈ አደረጃጃት ሲኖረው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የአማራ ህዝብ ጉዳዩች ላይ ሙሁራዊ ጥምረትን በፈጠረ መልኩ በትብብር ስራዎችን ይመራል፡፡
• ቁርጠኝነት፡- ተቋሙ እንደ ዓላማ ይዟቸው የተነሳባቸውን ጉዳዮች ከግብ ለማድረስ በሙሉ ቁርጠኝነት ይሰራል፡፡
• ዘላቂነት፡- ተቋሙ የተለያዩ አካላትን በማስተባበር ተጀምሮ የሚቀሩ ሳይሆን በዘላቂነት ለህዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትን ያከናውናል፡፡
የተቋሙ መሪ ቃል
ለልህቀት እንተጋለን!
የተቋሙ እሴቶች
- Home
- የተቋሙ እሴቶች

