የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለታለቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ድጋፍ አደረገ !
ጥቅምት 15/2008 ዓ.ም. በተለያዩ የሀገራችን ከተሞችና ወረዳዎች እየተዘዋወረ ያለው የህዳሴ ዋንጫ በሰሜን ጎንደር ወረዳዎች ሲዘዋወር ቆይቶ ጎንደር ከተማ በገባበት ወቅት ዩኒቨርሲቲውም ለዚህ ታላቅ ግድብ የበኩሉን ማድረግ ስለሚገባ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ከፊል ገፅታ
በዚህ ወቅት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት ዶክተር ታከለ ታደሰ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አገሪቱ ቀጣይነት ያለው የለውጥ ጎዳና ላይ እንደሆነች ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ታከለ ታደሰ የምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት
ሀገራችን ከግብርናው መር ክፍለ ኢኮኖሚ ወደ ኢንዱስትሪ መር ክፍለ ኢኮኖሚ እያደረገች ባለው ጉዞ የኤሌክትሪክ ሀይል እጅግ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህ ታላቅ ተግባር ታላቅ እቅድን ያዘጋጀችው ሀገራችን በራሷ ሀብትና በህዝቦችዋ ትብብር ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡ ለዚህ ግንባታ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ከምርምር ተግባራቱ ጎን በመሆን ከፍተኛ እገዛ እያደረገ ሲሆን በዕለቱ የአንድ ሚሊየን ብር ድጋፍ ከማድረጉ በተጨማሪ በ2008 ዓ.ም. ከሰራተኞች ደመወዝ ገንዘብ እያሰባሰብ በወር 1.1 ሚሊየን ብር ገቢ እያደረገ ይገኛል፡፡
ግድቡ የድህነትን አከርካሪ ለመስበር ታላቅ መሳሪያ በመሆኑ፤ የህብረተሰቡ ተሳትፎና ድጋፍ ለግድቡ መጠናቀቅም ከፍተኛ ጥቅም ስላለው መለው የሀገራችን ህዝብ ድጋፉን መቀጠል አለበት ሲሉ የምርምርና የህብረተሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዚዳንት አስረድተዋል፡፡
// የህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት//

