የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማህበረሰቡን የማገልገል ስራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል
የዩኒቨርሲቲው ዋንኛ ተልዕኮ ማለትም መማር ማስተማር፣ ችግር ፈች ምርምሮችን ማድረግና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት መሆናቸው ይታወቃል፡፡ የመማር ማስተማሩ ሂደት ጥራቱን የጠበቀና በተግባር የተደገፈ ለማድረግ ደግሞ በዩኒቨርሲቲው ያሉ ኮሌጆች፣ ፋካልቲዎች፣ ትምህርት ቤቶችና ኢንስቲቲውቶች የንድፈ ሀሳብ ትምህርቱን በመስክ ላይ ትምህርት(ስልጠና) ያስደግፋሉ፡፡ በተማሪዎች የመስክ ላይ ትምህርት ደግሞ ተማሪዎቹ በማህበረሰቡ ያሉ ችግሮችን ነቅሰው በማውጣት የማህበረሰቡን ችግር ይፈታሉ ሲፈቱም ቆይተዋል፡፡ በዚህም በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚደረገው የ TTP ፕሮጀክት ዋንኛ ተምሳሌት ነው፡፡

አሁን ደግሞ በማህበራዊና ስነ-ሰብ ኮሌጅ ስር የሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል የ2ኛዲግሪ ተማሪ የሆነው ይልማ ጌታነህ በጎንደር ከተማ አዘዞ ድማዛ ክፍለ ከተማ ለሚገኙ አቅመደካ ማአረጋዊያንና በጣም ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው የማህበረሰብ ክፍሎች መጠለያ የሚገለገሉ አስር ያህል ቤቶችን በመገንባት ላይ ነው፡፡ ተማሪ ይልማ ጌታነህ በመስክ ላይ ትምህርት ስልጠናው በአዘዞ ድማዛ ክፍለ ከተማ ከተመደ በበኋላ ወደስራ የገባው ከክፍለ ከተማው አመራሮችና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመወያየት የማህበረሰቡን ችግር በመለየት ነበር፡፡ ከውይይቱ ባገኘው ግብዓትም በጣም ዝቅተኛ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች ከፍተኛ የሆነ የመጠለያ ችግር መኖሩን ተረዳ፡፡ በዚህም ማህበረሰቡንና አጋር ድርጅቶችን በማሳተፍና በማስተባበር ወደ ተግባር ገብቷል፡፡

በመሆኑም ከክፍለ ከተማው የቦታና የባህርዛፍ እገዛ እንዲሁም ከኢትዮጲያ ቆርቆሮ ማምረቻ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር (Ethiopian steel PLC) ጎንደር ቅርንጫፍ ደግሞ 160 ቆርቆሮዎችን ማግኘት ችሏል፡፡
በአዘዞ ድማዛ ክፍለ ከተማ የማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ብርቱካን ሉሌ እና በክፍለ ከተማው የማህበረሰብ ድጋፍ ኃላፊ አቶ ማርቆስ በየነ ዩኒቨርሲቲው በሚያደርገው የማህበረሰብ አገልግሎት መደሰታቸውን ናተማሪውም ችግረኛ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለመርዳት የወሰደውን ቁርጠኝነትና ተነሳሽነት አድንቀዋል፡፡

አመራሮቹ አክለውም እነዚህ በመገንባት ላይ ያሉ ቤቶች በማህበረሰቡ ጥቆማ እና በሚመለከታቸው አካላት ለተመረጡ ግለሰቦ ችእንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡ ወደፊትም ክፍለ ከተማው ከዩኒቨርሲቲው ጋር እጅና ጓንት ሆኖ ለመስራት ያለውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

ተማሪው ያከናወነው ተግባር ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጎን መሆኑንና የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችም የበኩላቸውን እየተወጡ መሆናቸውን ያሳየናልና ሌሎች ተማሪዎችም የተማሪ ይልማ ጌታነህን ፈለግ በመከተል ማህበረሰቡን የማገልገል ተልዕኳችን ለማሳካት የጀመርነውን ጉዞ አጠናክረን እንቀጥል እንላለን፡፡

