የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት ለውይይት ቀረበ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክና የምርምር ዘርፎች የመዋቅር ማሻሻያ ጥናት የካቲት 09/2010 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ሰኔት አዳራሽ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል :: በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት፣ም/ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖችና ዳይሬክተሮች ተገኝተው በቀረበው የመዋቅር ጥናት ላይ የማስተካከያ ሀሳብ ሰጥተዋል ::
የመዋቅር ጥናቱ ዋና አላማ ዩኒቨርሲቲው የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮዎች ለማሳካት በሚያስችል ሁኔታ የአካዳሚክ፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች በሰለጠነና ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ለመስጠት የሚያስችል ዘላቂና ከወቅቱ ጋር አብሮ የሚሔድ መዋቅር ለማዘጋጀት መሆኑን የቀረበው ጥናት ያሳያል::
[widgetkit id=8387]
እንደ ጥናቱ አቅራቢዎች ገለፃም፣ የመዋቅር ማሻሻያ ጥናቱ መነሻ ያደረገው በየኮሌጁ የትምህርት ክፍሎች፣ የፕሮግራሞችና የተማሪወች ብዛት እየጨመረ መምጣቱና ይህም በተለያዩ ቢሮወች የስራ መብዛትና መደራረብ መፍጠሩን ፣ ዲን ፅ/ቤቶች በተለያዩ ውስብስብና ተመሳሳይ ስራዎች በመጠመድ፣ ለኮሌጆች ዕድገት ስልት ለመንደፍ የጊዜ እጥረት መግጠሙን፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ተግባራት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መሔዱን እና ሌሎችንም ጉዳዮች መሰረት በማድረግ ነው :: የመዋቅሩ ጥናት ነባሩ የአካዳሚክ፣ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፎች ያሉበትን ክፍተቶች በማየትና በመለየት፣ ከኮሌጆችና ዳይሬክቶሬቶች ጋር ሰፊ ውይይት በማድረግ ፣በዩኒቨርሲቲውና በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚተገበሩ የለውጥ አቅጣጫዎችን ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት፣ የሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችን መዋቅር በድረ -ገፃቸው አመካኝነት በማየትና በመገምገም የተዘጋጀ ነው ::
በደስታው ዋኘው
አርታኢ፡ይዳኙ ማንደፍሮ
የህ/ዓ/አ/ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

