የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኛ ሰራተኞች ማህበር ውይይት አካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኛ ሰራተኞች ማህበር አመሰራረትና አጠቃላይ እንቅስቃሴን አስመልክቶ የማህበሩ አባላት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ጥር 26/2010 ዓ.ም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲ.ቢ.አር/CBR ፕሮግራም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሂዷል፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኛ ሰራተኞች ማህበር ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሲ.ቢ.አር ፕሮግራም በተደረገ ድጋፍ እና ከዩኒቨርሲቲው የድጋፍ ደብዳቤ በማጻፍ ከሰሜን ጎንደር ዞን አስተዳደር ፀጥታና ፍትህ ጽ/ ቤት የምዝገባና ፈቃድ ዕውቅና በማግኘት በ2008 ዓ.ም እንደተመሰረተ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
[widgetkit id=8254]
በዩኒቨርሲቲውና ከዩኒቨርሲቲው ውጪ ለሚገኙ አካል ጉዳተኞች በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዙሪያ የሚያጋጥማቸውን ችግሮች በመፍታት፣ ያላቸውን እውቀትና ክህሎት በማደበር፣ ለሀገራቸው የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንዲያረክቱ ማድረግ፣ መማር መለወጥ እየቻሉ ነገር ግን በተለያዩ ምክንያቶች እድሉን ላአላገኙ አካል ጉዳተኞች በማህበር በማደራጀት ተጠቃሚ ማድረግን ተልዕኮ አድርጎ የተነሳ ማህበር እንደሆነ የማህበሩ ሊቀ መንበር አቶ ምስጋናው ሰማኝ ገልጸዋል፡፡
በዕለቱ የማህበሩ መመስረት የሚያስገኛቸው ጠቀሜታዎች፣ ማህበሩ የሰራቸው ስራዎች፣ የማህበሩ ጠንካራና ደካማ ጎን፣ ስለ ቀጣይ እቅዶች እና ተያያዥ ስለ ሆኑ ጎዳዮች ውይይት ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም “የአካል ጉዳተኛ ሰዎች ቅጥር፣ መብት፣ የስራ ስምሪት በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ምን ይመስላል/THE RIGHT TO WORK AND EMPLOYMENT OF PERSONS WITH DISABILITIES IN ETHIOPIA: THE CASE STUDY OF UNIVERSITY OF GONDAR?” የሚል ጥናታዊ ጹሁፍ በአቶ አዱኛ ታረቀኝ ቀርቧል፡፡ የቀረበውን ጥናታዊ ጹኅፍ መነሻ በማድረግ ተሳታፊዎች ውይይት አድርገዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አምሳሉ ግዛቸው
የህዝብና ዓለም አቀፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር

