የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን እየሰጠ መሆኑ ተገለጸ

የዓፄ ቴወድሮስ ግቢ ተማሪዎች የግዕዝ ቋንቋን በመ/ር ፀዳሉአዲሱ ሲማሩ፡፡
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብ ኮሌጅ የኢትዮጵያ ቋንቋዎችና ሥነጽሑፍ ትምህርት ክፍል የግዕዝ ቋንቋ ትምህርትን ለዩኒቨርሲቲው ማህበረ-ሰብ እየሰጠ መሆኑን የግዕዝ ቋንቋ ትምህርቱን በበላይነት የሚያስተባብሩት መ/ር ፀዳሉ አዲስ እና መ/ርሰንኮሪስ አያሌው ገልጸዋል፡፡ እንደ አስተባባሪዎቹ ገለጻ፣የግዕዝ ትምህርቱ በማራኪ፣ በዓጼ ቴወድሮስና በዓጼ ፋሲል፣በ3ቱም ግቢዎች እየተሰጠ ያለ ሲሆን በቀሪዎቹ የመለስ ዜናዊ እና ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ2ቱም ግቢዎች ምዝገባው ተጠናቆ በህዳር ወር ውስጥ ትምህርቱ እንደሚጀምር ገልጸዋል፡፡

የማራኪ ግቢ ተማሪዎች የግዕዝ ቋንቋ ሲማሩ፡፡

የዩኒቨርስቲው ማኅበረ-ሰብእ የግዕዝ ቋንቋን በመ/ር ሰንኮሪስ አያሌው ሲማሩ የሚያሳይ፡፡
አስተባባሪዎቹ አያይዘው የግዕዝ ቋንቋ ትምህረቱ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለዩኒርሲቲው ማህበረ-ሰብ መሰጠት መጀመሩ ለጎንደር ማህበረ-ሰብ ብሎም ለኢትዮጲያ ወግና ባህል መዳበር የሚረዳ ከመሆኑም ባሻገር ለጥናትና ምርምር ሥራም ከፈተኛ የሆነ ማህበረ-ሰባዊ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ህዳር17/2008ዓ.ም የቅኔና ሥነ-ጽሑፍ ምሽት ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ እንደሚካሄድና የዩኒቨርሲቲው ማህበረ-ሰብም በዚህ ዝግጅት ተሳታፊ እዲሆን አስተባባሪዎቹ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በእየሳምንቱ ቅዳሜ ከ2 ሰዓት ጀምሮ የሚሰጠውን የግዕዝ ቋንቋ ትምህርቱን አሰመልክቶ ያነጋገርናቸው 3 የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አባላት የግዕዝ ቋንቋ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ መሰጠት መጀመሩ ቋንቋውን ከማሳደግ አልፎ ቋንቋውን አስመልክቶ የጥናትና ምርምር ሥራን ለመሥራት የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የዓፄ ቴወድሮስ ግቢ ተማሪዎች በቅኔና ግዕዝ ትምህርት ላይ፡፡

የአፄ ቴዎድሮስ ግቢና የማራኪ ግቢ ከፊል ገፅታ፡፡
የቅኔና ሥነ-ጽሑፍ ምሽት ዝግጅቱን አሰመልክቶ የተነገሩ የግዕዝ ቋንቋዎችና የቅኔ መዎድሶች እስኪ ትንሽ እናቅርብላችሁ፡፡
ልሳነ-ግዕዝ
በከመ ይቤሉ ምሁራን በእንተ ረብዓ ግዕዝ፣ወንሕነ ንፈቅድ ተናግሮ ሕዳጠ በእንተ ልሳነ-ግዕዝ፡፡
ኦ አንትሙ ሕዝበ-ጎንደር ወሕዝበ-ዓቢይ መካነ-ትምህርት ዘጎንደር፣ እስኩ አጽምዑ መርሐ ግብርነ ዘልሳነ-ግዕዝ በበሀለውክሙ ኩለሄ፡፡
ልሳነ-ግዕዝ ብሂል ልሳነ-ምስጢር ውእቱ፣ ወበእንተዝ ዝንቱ ልሳን ዐቢይ ረብዕ ሀሎ በብሄረ ጎንደር ወኢትዮጵያ ለሐታቴ ጥበብ ወሕክምና፣ ለታሪክ ወለሥነ ጽሑፍ፣ ለሥነ ፈለክ ወለ ኁልÖዕ ዘመን ወበእንተዝ እምነ ወርሐ ሕዳር ፳፻ô ዓ.ም ወጢኖ ኩልክሙ ንዑ ወተሳትፉ ለሚሂረ ለሳነ-ግዕዝ እምነ ዐቢይ መካነ-ትምህርት ዘጎንደር ወከመ ንሕጽኖ ኅቡረ ለልሳነ-ግዕዝ እስመ ቦቱ ጥበብ ውስቴቱ፡፡ ዝንቱ ውዕቱ መልዕክትነ፡፡
ትርጉም
ሥለ ግዕዝ ጥቅም ብዙ ምሁራን እንደተናገሩት ሁሉ እኛም ስለግዕዝ ቋንቋ የተወሰነ መናገር እንፈልጋለን፡፡ የጎንደር ሕዝብና የጎነደር ዩኒቨርሲቲ ማህበረ-ሰብእ በሙሉ እስኪ የግዕዝ ቋንቋ ፕሮግራማችንን ዘወትር በእያላችሁበት ሆናችሁ ተከታተሉ፡፡ የግዕዝ ቋንቋ ማለት የምሥጢር ቋንቋ ማለት ነው ስለዚህ ይህ የሚስጥር ቋንቋ በጎንደር አካባቢና በኢትዮጵያም ጭምር ለሕክምና፣ ለምርምር፣ ለታሪክ፣ለሥነ ጽሑፍ፣ለዘመን አቆጣጠርና ለሥነ ፈለግ የጥበብ ሥራ ከፍተኛ የሆነ ጥቅም አለው፡፡ ስለዚህ ከህዳር2008 ዓ.ም ጀምሮ ሁላችሁም በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በሚሰጠው የግዕዝ ቋንቋ ትምህርት ተሳታፊ ሁኑ እና የግዕዝ ቋንቋን በጋራ እናሳድገው መልዕክታችን ነው፡፡
ጉባኤ ቃና ቅኔ፡-አበ ልሳናት ግዕዝ መሰረትን ለኩሉ፣
ጎንደር ከመ ኢይርሳእከ መሐለ በቃሉ፡፡
ትርጉም፡– ለሁለመናችን መሠረት የሆንከው የቋንቋዎች አባት ግዕዝ ሆይ ጎንደር እንደማይተውህ በቃሉ ምሎልሃልና ደስ ይበልህ፣ ግዕዝ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዕውን ይሆናል፡፡
ዋዜማ ቅኔ፡– ተፈስሒ ጉባኤነ ወላዲተ-ልሳን ግዕዝ እንተ ወለደ ቅኔኪ፣
እምኔኪ አምጣነ ተወልደ ውስተ-ጎል ማራኪ፣
ከመ ተነበዩ ቅድመ ኃሠሥተ ልሳን ሕዝብኪ፣
ወበ ነቢያት ጠበብት ጠበብተ ቤትኪ፣
ትንቢቶሙ ተፈጸመ ብኪ፡፡
ትርጉም፡-ዩኒቨርሲቲያችን ጎንደር ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ የግዕዝ ህጻን መወለድን የሚፈልጉ ነቢያት ምሁራን እንደ ትነቢት መላ ምታቸው ግዕዝ ህጻን ከአንች ተወልዷልና/ተጀምሯልና/ ደስ ይበልሽ፡፡

ወደ ማራኪና ዓፄ ቴዎድሮስ ግቢዎች የሚወስዱት መንገዶች፡፡

