የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን ደጋፊዎች ማህበር አባላት፣ የየግቢ ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን መረጡ፡፡
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተወዳጅና አንጋፋ ለሆነው ለፋሲል ከነማ የእግር ኳስ ቡድን የምን ጊዜም አጋር መሆኑ ይታወቃል፣ በመሆኑም ይህንን አጋርነቱን ይበልጥ ለማጎልበት ተቋሙ በስሩ የሚገኙ የተለያዩ ክፍሎችን በፈቃደኝነት በማስተባበር፣ የካቲት 30/2010 ዓ.ም በአጼ ቴወድሮስ ግቢ የተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ በተደረገ ውይይት ቡድኑን በማናቸውም መልኩ ለመደገፍ፣ 7 የየግቢው ዋና ስራ አስፈጻሚዎችን በመምረጥ የደጋፊዎች ማህበር ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አቋቁሟል፡፡
• ከአፄ ቴዎድሮስ ግቢ …………………. አቶ ዳዊት ዳርጌና አቶ አለማየሁ ታደሰ
• ከማራኪ ግቢ …………………………….. አቶ ሳሙኤል ገብሩ
• ከህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ……… አቶ ቻሌ አስማረ
• ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት …………….. አቶ ሄኖክ ዮንስ
• ከግብርናና ገጠር ትራንስፎርሜሽን ኮሌጅ……… አቶ አስራት አየለ
• ከኮሚኒቲ ት/ት ቤት …………………………………… አቶ መንግስቱ ሙሉ – በዋና ስራ አስፈጻሚነት ግቢወችን ወክለው እድዲሰሩ በጠቅላላ ጉባኤው ሀላፊነት ተሰጥቷቸዋል፡፡
ተመራጮችም ቡድኑን በቅንነትና በታማኝነት በማገልገል የተሰጣቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ በሙሉ ልብ ቃል ገብተዋል፡፡
ሁሌም ከፋሲል ጋር ነን
ድል – ለፋሲል ከነማ !
ዘጋቢ፡- አምሳሉ ግዛቸው

