ጎንደር ዩኒቨርሲቲ በድጋሚ አንደኛ ወጣ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ35ኛው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥቅምት 6/2010 ዓ.ም ጀምሮ በተካሄደው ጉባኤ በ2009 ዓ.ም በነበረው አጠቃላይ አፈፃፀም ከነባር ዩኒቨርሲቲዎች አንደኛ በመውጣቱ ከፍተኛ ደስታ ተሰምቶኛል፡፡ ከምንም በላይ ባለፈው አመት በተመሳሳይ የተገኘውን የአንደኝነት ደረጃ ማስጠበቁ ውጤቱን የተለየ ያደርገዋል፡፡
ለዚህ ውጤት የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ሰራተኞችና አጋር አካላት በጋራ ሰፊ ውጤታማ ስራ ሰርታችኋልና በእጅጉ አመሰግናለሁ፡፡ ከዚህ በተሻለ ወደፊት አብረን እንደምንሰራ እምነቴ ፅኑ ነው፡፡
እንኳን ደስአለን እንኳን ደስ አላችሁ፡፡
አቶ ተፈራ ደርበው
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ

