ፕሮፌሰር ተገኝ ገ/እግዚአብሄር የከተሞች መስፋፋትና የከተማ ገጠር ትስስር በኢትዮጵያ (Urbanization and Linkages with Rural Economies in Ethiopia) የሚል ጥናታዊ ፅሁፍ አቀረቡ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የጂኦግራፊና አካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ማራኪ ግቢ ከአዲሱ ህንፃ በኮሌጁ አዳራሽ ጥር 24/2010 ዓ/ም ሴሚናር አካሄደ፡፡የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሰረት ካሴ ፣ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ የኮሌጁ መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች በተገኙበት እውቁ የከተማ ልማትና እቅድ ተመራማሪ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር የሆኑት ፕ/ር ተገኝ በኢትዮጵያ በከተሞች እድገትና የከተማ ገጠር የኢኮኖሚ ትስስር ያለውን ሚና እና ተግዳሮት ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ግንዛቤ መፍጠርን አላማ ያደረገ የመወያያ ፅሁፋቸውን አቅርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
[widgetkit id=8223]
ኮሌጁ ከአሁን በፊትም በርካታ ሴሚናሮችን በማካሄድ፣ ምሁራንን በመጋበዝ በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ የተሰሩ ጥናታዊ ፅሁፎች እንዲቀርቡ በማድረግ፣ ልምዳቸውንና እውቀታቸውን ለዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ ተመራማሪዎችና ተማሪዎች እንዲያካፍሉ ሰፊ ስራ ለመስራት ችሏል ፡፡
በመጨረሻም ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ ፕ/ር ተገኝ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመምጣት እውቀታቸውን ለማካፈል ፈቃደኛ በመሆናቸው በኮሌጁ ስም አመስግነው፣ ያቀረቡት ጥናት እውቀትን ከማስተላለፍ ባሻገር ለተመራማሪዎች፣ ለሁለተኛ ዲግሪና ለፒ.ኤች.ዲ ተመራቂ ተማሪዎች ወደፊት ጥናታዊ ፅሁፎቻቸው መነሻ የሚሆኑ ሀሳቦችን እንደሚያገኙ ተስፋ አደርጋለሁ በማለት ሴሚናሩ ተጠናቋል ፡፡

