በአዘዞ አካባቢ እየተገነባ ያለው የእናቶች ማዋለጃ በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል
በስፔን ሀገር የሚገኙ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች ሀላፊዎች አዘዞ አካባቢ ተገንብቶ በመጠናቀቅ ላይ የሚገኙውን የእናቶች የማዋለጃ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችል ነጥቦች ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ ጋር ተወያዩ፡፡

የፕሮጀክቱ ሀሳብ አፍላቂና ዋና አስተባባሪ የሆነችው ትዉልደ ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ የሺ በየነ ነዋሪነቷ እስፔን ሀገር ሲሆን “እናታችን እንርዳ” የሚል ፕሮጀክት በመቅረጽ እስፔን ሀገር ከሚገኙ ሁለት ድርጅቶች (Mensajero de la Paz እና principe de Asturias) ፈንድ በማግኘት ማዕከሉን ከመገንባት ጀምሮ አሁን እስካለበት ደረጃ ድረስ የአምቡላንስና የተለያዩ ድጋፎችን ስታመቻች የቆየች ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊት ነች፡፡ በተመሳሳይ ወ/ሮ የሺ የMensajero de la Paz ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ዋን ሚጌል እና የprincipe de Asturias ዳይሬክተር የሆኑት ሲሜና ዩነዱን ይዛ በመምጣት ለጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕረዝዳንት ለዶ/ር ደሳለኝ መንገሻ እና ለዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ደ/ር ይንገስ አለሙ ማዕከሉ ስራ ሲጀምር ለማዕከሉ ግልጋሎት የሚዉሉ 6 አውቶብሶችን በተጨማሪም ለመለገስ የካቲት 8/2009 ዓ.ም ቃል ገብተዋል፡፡ የጎንደር የኒቨርሲቲ ወደ ጤና መዕከሉ የሚወስድ የኮብልስቶን መንገድ በመስራት ላይ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዩኒቭሲቲው እና ድርጅቶቹ ለወደፊትም በጋራ ሲለሚሰሩባቸዉ ጉዳዮች ተመካክረዋል፡፡


ዘጋቢ፡- አምሳሉ ግዛቸው

