ሰላም የባህል መድረክ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ታህሣስ 20/2012 ዓ.ም እየተካሄደ ይገኛል።

ውይይቱ በኪነጥበብ ዘርፍ በተለይም ‘የአዝማሪ ሚና ትናንት፣ ዛሬና ነገ’ በሚል ርዕስ ትኩረት ያደረገ ነው። ጎንደር ዩኒቨርሲቲ፣ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲና ሰላም ኢትዮጵያ ፕሮግራሙን በጋራ አዘጋጅተውታል። የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ዶ/ር አነጋግረኝ ጋሻው፣ የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ም/ኃላፊ አቶ እድሪስ አብዱ፣ ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ አዝማሪዎች፣ የዘርፉ ምሁራንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የውይይቱ ተሳታፊዎች ናቸው። ዝርዝር ዜናውን በስፋት እንመለስበታለን።



