የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ድህረ-ምረቃ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወርሃዊ ሴሚናር አካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ድህረ-ምረቃ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ወርሃዊ ሴሚናር አካሄደ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ድህረ-ምረቃ ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ታህሳስ 24/2012ዓ/ም ወርሃዊ ሴሚናር በማራኪ ግቢ አልሙኒዬም ህንፃ አዳራሽ አካሄደ፡፡ ሴሚናሩ የተካሄደው በድህረ-ምረቃ ጥናትና ምርምር ዙሪያ ሲሆን፣ ከድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና ከግቢው ማህበረሰብ ጋር ምክክር ተካሂዷል፡፡

በሴሚናሩ የዩኒቨርሲቲው የድህረ ምረቃ ማሰተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ፣ የኮሌጁ ዲን ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ፣ የኮሌጁ መምህራን፣የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተገኝተዋል፡፡

ኮሌጁ በድህረ ምረቃ ጥናትና ምርምር ዙሪያ ሴሚናር ማዘጋጀቱን በማድነቅ ወደፊትም ያለውን ሰፊ የሰው ሀይል በመጠቀም ተከታታይነት ያለው ሴሚናር ማካሄድ እንደሚኖርበት የዩኒቨርሲቲው የድህረ ምረቃ ማሰተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሳህሌ በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡

በመቀጠል በአቶ ሙሉቀን አበራ እና በፕሮፌሰር አሌክሳንደር ራጁ ሁለት ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው በርካታ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡



