ብሄርተኝነትና ይዘቶቹ በሚል ሴሚናር ተካሂዷል
ሴሚናሩ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ አዘጋጅነት ጥር 01/2012ዓ/ም በአልሙኒዬም አዳራሽ ተከሂዷል፡፡

በዚህ ሴሚናር ዲኖች፣ ዳይሬክተሮችና መምህራን የተገኙ ሲሆን፣ የሶሻል አንትሮፖሎጅ መምህር የሆኑት ዶ/ር ተባባር ጫኔ የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ በአደረጉት የመክፈቻ ንግግር ፕሮግራሙ ተጀምሯል፡፡
የዚህ ሴሚናር ዋና አላማም የአማራ ብሄርተኝነት እንቅስቃሴን በአካዳሚክ ምሁራዊ መድረክ ውስጥ እንዲቀርብ በማድረግ ውይይት ማካሄድና ወደ ፊትም በጥናትና ምርምር የተደገፈ የመፍትሄ ሀሳቦች ለማምጣት እንደሆነ በመድረኩ ተገልጿል፡፡

በመድረኩ ጥነታዊ ፅሁፉን ያቀረቡት ከአዲስ አበባ የሳይንስና ቴክኖሎጅ ዩኒቨርሲቲ መምህር ዶ/ር ቴዎድሮስ ሃይለማሪያም ሲሆኑ የአማራ ብሄርተኝነት እንደ ሌሎቹ ብሄር ብሄረሰቦች የነገድ ወይም የጎሳ ሳይሆን ጠንካራ በሆነ ታሪካዊና ባህላዊ ትውፊቱ እንደሆነ በፅሁፋቸው ገልፀዋል፡፡

በመጨረሻም የአማራ ብሄርተኝነት ጥያቄ እንዴት መጠናከር እንዳለበትና ጥያቄው ተገቢ ነው ወይስ አይደለም በሚል ጥያቄዎች ተነስተው ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ፕሮግራሙ ተጠናቋል፡፡



