በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበረሰብ ጥናት ላይ ያተኮረ ሴሚናር ተካሄደ
ጥር 29/2012 ዓ.ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም የመሰብሰቢያ አዳራሽ በህብረተሰብ ጥናት ላይ ያተኮረ ሴሚናር ተካሄዷል፡፡ በሴሚናሩም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በሳይኮሎጅ ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑት ዶ/ር አዕምሮ አስማማው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ካደረጉ በኋላ የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር ካሳሁን ባደረጉት ንግግር ትምህርት ቤት ውስጥ ገብቶ በመማር ከሚገኘው ዕውቀት ባልተናነሰ በተለያዩ ሴሚናሮች የምናገኛቸው ጠቃሚ ተሞክሮዎች እንዳሉ የገለፁ ሲሆን በቀጣይም እንዲህ ዓይነቱ ሴሚናር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ በዚህ ሴሚናር ልምዳቸውን ያካፈሉት የካናዳ ዜግነት ያላቸውና በካናዳ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት ውስጥ በማህበረሰብ ፖሊሲ በአማካሪነት እየሰሩ የሚገኙት አቶ አስረዳው ዘውዱ ሲሆኑ በካናዳ ውስጥ በሚገኘው የካርሌቶን ዩኒቨርሲቲ የ2ተኛ ዲግሪያቸውን አግኝተዋል፡፡
ህዝብና ዓለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



