“ቅርሶቻችንን በዩኔስኮ ከማስመዝገብ በፊት በትውልዱ አእምሮ ውስጥ ማስመዝገብ ይቀድማል”
የጎንደር የኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትም/ክፍል ከማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ማህበረሰብ አገ/ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር መተባባር ለቅርስ ጥበቃ ባለድርሻ አካላት የካቲት 28ና 29/2012 ዓ.ም በግብርናና ገጠርት ራንስፎርሜሽ ኮሌጅ አዳራሽ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በአለምአቀፋዊና ሀገር አቀፋዊ የቅርስ ህጎችና የቅርሶች አስተዳደር ላይ ትኩረት ባደረገው በዚህ ስልጠና፣ 50 የሚሆኑ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የተወጣጡ የቅርስ አስተዳደር ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትም/ክፍል መምህርና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ሸጋለም ፍቃዱ ፣ የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በደባርቅ ማዕከል የተሰጠ ሲሆን በጠዳ ማዕከል የተሰጠው ሁለተኛው ዙር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ እንደ አስተባባሪው ገለጻም፣ የቅርስ አስተዳደርን እውን ለማድረግ ሶስት መሰረታዊ ሁኔታዎች ያስፈልጋሉ፡ ተቋም፣ህግና ሀብት፡፡

ከእነዚህ መሰረታዊ ሁኔታዎች መካከልም በዚህ ስልጠና ህግ ላይ ትኩረት በማድረግ ዘላቂ የቅርስ አስተዳደርን እውን ለማድረግ መደረግ ያለባቸውና የሌላባቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት ሰፊ ግንዛቤ ለመፍጠር ታልሞ ስልጠናው መሰጠቱን መ/ር ሸጋለም ፍቃዱ አብራርተዋል፡፡

አንዳንድ የስልጠናው ተሳታፊዎች እንደገለጹት፣ ህብረተሰቡ ስለቅርሶች ጠቀሜታ በአግባቡ እንዲያውቅ ቢሰራ ቅርሶቹ እንዳይሰረቁ፣ እንዳይጎዱና እንዳይጠፉ ህዝቡ ይንከባከባቸዋል፡፡የርዕሰ አድባራት አዘዞ ተ/ኃይማኖት ወ ቅ/ገብርኤል አድባራት አስተዳዳሪ ፀባቴ መሰረት ባንታየሁ እንደገለጹት፣በሀገር አቀፍም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ የታወቁ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶቻችን መገለጫወቻችን ናቸው፤ ሆኖም ይላሉ ፀባቴ መሰረት ባንታየሁ ፣ “ቅርሶቻችንን በዩኔስኮ ከማስመዝገብ በፊት በትውልዱ አእምሮ ውስጥ ማስመዝገብ ይቀድማል”
የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



