በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ልዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅት ተካሂደ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍልና የባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል ትብብር ’’ሰላምና ኪነ-ጥበብ’’ በሚል ዋና ሃሳብ የተዘጋጀ ኪነ-ጥበባዊ ድግስ የካቲት 2/2012 ዓ.ም በማራኪ ግቢ አልሙኒየም አዳራሽ ተካሂዷል፡፡

በዝግጅቱ የኮሌጁ መምህራንና በርካታ ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን በሶሻል ወርክ ትምህርት ክፍል የፒኤችዲ /PHD/ ፕሮግራም አስተባባሪ ዶ/ር አዱኛ አበበ ፕሮግራሙን በንግግር አስጀምረዋል፡፡

በዚህ ዝግጅት የቲያትር፣ ጥበባትና ፊልም ፕሮዳክሽን፣የሙዚቃ ትምህርት ክፍሎችና የዩኒቨርሲቲያችን ባህልና ኪነ-ጥበብ ማዕከል መምህራንና ተማሪዎች የተዘጋጁ መሳጭና አገራዊ አንድነትን ሊሰብኩ የሚችሉ ግጥሞች፣ መጣጥፎች ፣ ጭውቶች፣ መነባንቦችና ፊልሞች ለታዳሚዎች ቀርበዋል፡፡

ዋና ዓላማው በልዩ ልዩ ኪነ-ጥበባዊ ዝግጅቶች እየተዝናኑ ሰላምን ለመስበክ የተዘጋጀ ፕሮግራም መሆኑን የዝግጅቱ አስተባባሪዎችና የ2ኛ ዓመት የፒኤችዲ /PHD/ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዳልካቸው ታየ፣ ሄለን አሥራትና ሰጠኝ አሊ ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም ለዝግጅቱ መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ለዩኒቨርሲቲያችን የተማሪዎች ህብረት፣ የሰላም ፎረምና የተማሪዎች አገልግሎት አባላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ይህ ዓይነቱ ዝግጅት ቀጣይነት እንዲኖረው ተሳታፊዎች አሰተያየት ሰጥተዋል፡፡
የሕዝብና ዓለም ቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



