’’ሥልጠናዊ የግምገማ መርሃ-ግብር’’ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የ2012 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2013 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ በተመለከተ ከሃምሌ 30/2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት የሚቆይ ’’ሥልጠናዊ የግምገማ መርሃ- ግብር’’ መካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

በዚህ ’’ሥልጠናዊ የግምገማ መርሃ- ግብር’’ ፕሬዚዳንቶች፣ ዲኖች፣ም/ዲኖች፣ዳይሬክተሮችና የጽ/ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው መስቀለ-ቃል ፕሮግራሙን በማስተዋወቅ እንኳን ደህና መጣችሁ ካሉ በኋላ፣ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት ዓፀደ-ወይን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

ዶ/ር አሥራት በንግግራቸው የበጀት ዓመቱ ከወትሮው በተለየ ፈታኝ እንደነበር እና ከተማሪ አቀባበል ጀምሮ እስከ የመጀመሪያው ወሰነ-ትምህርት ድረስ ዩኒቨርሲቲው ኃላፊነቱን በብቃት እንደተወጣ አንስተዋል፡፡

በተጨማሪም ተማሪዎች ወደ ቤተሰቦቻቸው ከተመለሱ በኋለም በኮቪድ-19 (የኮረና ተዋህሲ) ላይ የተደረገውን የድጋፍ እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ ፕሬዚዳንቱ አድንቀው፣ በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ የተደረገውን ድጋፍ አንዱ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ ደረጃ የመጀመሪያውን የተማሪዎች የምረቃ መርሃ-ግብርን በበይነ-መረብ /Virtual/ ማካሄዱ በዩኒቨርሲቲው ያለውን ጠንካራ አፈጻጸም የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

የሕዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬትጎንደር ዩኒቨርሲቲሃምሌ30/2012 ዓ.ምሐገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!



