የእንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የውልቸርና የክራች ድጋፍ ተደረገ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የአካል ጉዳተኞች ጥናትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት በአካል ጉዳታቸው ምክንያት ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ለተቸገሩ – የእንቅስቃሴ ችግር ላለባቸው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ት/ት ቤት ተማሪዎች የዊልቸር (የመንቀሻ ወንብር) እና የክራንች (የድጋፍ በትር) ድጋፍ አድርጓል፡፡ የዩኒቨርሲቲው የአካል ጉዳት ጥናትና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አስቴር አስራትና የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰለሞን ፈንታው በጎንደር ከተማ ሴቶች፣ ወጣቶችና ህጻናት ቢሮ ታህሳስ 2/2013 ዓ.ም ተገኝተው የዊልቸርና ክራንች ስጦታውን አበርክተዋል፡፡
አካልጉዳተኛ ተማሪዎችን ለዩኒኒቨርሲቲ ለማብቃት ከአንደኛ ደረጃ ጀምሮ መርዳትና መደገፍ ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር አስቴር አስራት በተቻላቸው መጠን ድጋፋቸው እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡ የዩኒቨርሰቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሰለሞን ፈንታውም በበኩላቸው በጎንደርና አካባቢዋ የሚገኙ አካልጉዳተኞችን በተለያየ ዘርፍ እየረዱ እንደሆነ ገልጸው ተማሪዎችን ብቻ ሳይሆን ስራ በመፈለግ ላይ ያሉትንም ጭምር በማደራጀት የስራ እድል እየፈጠሩ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
የጎንደር ከተማ የሴት አካልጉዳተኞች ማህበር ፕሬዝዳንት የሆኑት በላይነሽ ሲሳይ፣ የሴቶች ወጣቶችና ህጻናት ሀላፊ የሆኑት በለጡ መንግስቴና የጎንደር ከተማ ሴቶች ፌዴሬሽን ሀላፊ የሻረግ አብድርሀማን እንደዚህ አይነት ድጋፍ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቅሰው ቀጣይነት እንዲኖረው በማሳሰብ ተረክበዋል፡፡
************
ሀገራችንን ለማገልገል ቆርጠን ተነስተናል!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት







