2ኛ ዙር የስትራቴጅክ እቅድ ዝግጅት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት የስትራቴጅክ እቅድ ዝግጅት በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ከግንቦት 10-13/2013 ዓ.ም በጎንደር ኦሎምፒክ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተሰጠ ፡፡

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 5 ዓመታት በሀገራችን ቀዳሚ ከሚባሉት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ አንዱ በመሆኑ በትምህርት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የጥራት ሽልማት ድርጅት እውቅናና ሽልማት በተደጋጋሚ እንደተበረከተለት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን በመክፈቻ ንግግራቸው አስታውሰዋል፡፡ አያይዘውም የስልጠና ሀሳቡን ከማፍለቅ ጀምሮ እስካሁን በሃላፊነት ስልጠናውን እያስተባበረ ለሚገኘው ለእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት የ10 አመቱን ስትራቴጅክ እቅድ አዘጋጅቶና አፀድቆ ወደ ሁሉም ፈፃሚ አካላት በማውረድ የካስኬዲንግ ስራ እንዲሰራ ለማድረግ ይህ ሁለተኛ ዙር ስልጠና በአስተዳደር ዘርፍ ለሚገኙ የእቅድ አዘጋጅ የመካከለኛ አመራሮች እና በየስራ ክፍሉ ለተመለመሉ የስትራቴጅክ እቅድ ዝግጅት ኮሚቴ አባላት እየተሰጠ እንደሚገኝ የእቅድና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ጋሻው ነበሩ ገልፀዋል፡፡

የመጀመሪያው ዙር ስልጠና ከግንቦት 3-6/2013 ዓ.ም መሰጠቱ ይታወሳል፡፡



