ዩኒቨርሲቲያችን የ5ኛው አገር አቀፍ የህግ ትምህርት ቤቶች አምሳለ ችሎት ቤት (National Moot Court) ውድድር አሸናፊ ሆነ።
የጎንደር ዮኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ለ5ኛው ዙር በአገር አቀፍ ጀረጃ በድሬዳዋ ዮኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በተደረገው የኢትዮጵያ ህግ ትምህርት ቤቶች ውድድር አሸናፊ በመሆን ለውድድሩ ከተዘጋጁት አራት ዋንጫዎች ሶስቱን በመውሰድ አሸንፏል። በዚህ መሰረት፦
1. ተማሪ ትንሳኤ ብርሀን ንጉሱ የውድድሩ ማጣሪያ ምርጥ ተናጋሪ፣
2. ተማሪ ዮሴፍ ነበሩ የውድድሩ ምርጥ ተናጋሪ እና
3. የአጠቃላይ ውድድሩ አሸናፊ በመሆን አንጸባራቂ ድል አስመዝግበዋል።

የጎንደር ዮኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት በዚህ ውድድር ባለፈው አመት ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀ ሲሆን በአገር ውስጥም ሆነ በተለያዮ ውጭ ሀገራ የአምሳለ ፍርድ ቤቶች/ችሎት ውድድሮች በተደጋጋሚ የአገራችን ስም ማስጠራቱ ይታወቃል።
ትምህርት ቤቱ በማህበረሰብ አገልግሎት ለአቅመ ደካሞች፣ ለሴቶች፣ ሕጻናት እና ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች ነጻ የህግ ድጋፍ አገልግሎት በመስጠትም ይታወቃል።




