የፒ.ኤች.ዲ(PhD) ሳምንት ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሰቲ ተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከባዮሎጂ ት/ክፍል ጋር በመተባበር ግንቦት 23 እና 24/2013 ዓ.ም የፒ.ኤች.ዲ(PhD) ሳምንት በአጼ ተዎድሮስ ግቢ ድህረ ምረቃ አዳራሽ አካሄደ፡፡

የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር ወርቁ ነጋሽ፣ የዩኒቨርሲቲው ድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ዳይሬክትር ዶ/ር አስማማው አለሙ፣ በኮሌጁ የሚገኙ ፕሮፌሰሮች እንዲሁም ጀማሪ ተመራማሪዎችና መምህራን በፕሮግራሙ ላይ ተሳትፈዋል ፡፡
ደ/ር ወርቁ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲንን በመወከል የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸውም በ2008/9 ዓ.ም ውስን የፍልስፍና ዲግሪ ተማሪወች የነበሩት የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በአሁኑ ጊዜ በርካታ የፒኤዲ ተማሪዎችን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር አስማማው በበኩላቸው ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት የጎንደር ዩኒቨርሰቲ በዋናነት የጥናትና ምርምር ተቋም እንደመሆኑ መጠን ለድህር ምረቃ ፕሮግራሞች የበለጠ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡ ስለሆነም በዩኚቨርሲቲው ከ 148 በላይ የሁለተኛ ዲግሪ (Masters Program) እንዲሁም 35 በላይ የሶስተኛ ዲግሪ (PhD) ትምህርት መርሀ ግብሮች እየተሰጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

በኮሌጁ ያሉ ክፍተኛ ተመራማሪዎችና መምህራን (professors) እንዲሁም ጀማሪ ተመራማሪዎችና መምህራን (graduate assistants) እርስ በእርስ የሚማሩበት ሳምንት እንደሆነ ከኮሌጁ ድህረ ምረቃ ማስ/ጽ/ቤት አስተባባሪ ከዶ/ር አጥናፉ ጓዴ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡



