በተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የሶፍት ዌር ስልጠና ተሰጥቷል
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት እና የምርምርና ህትመት ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በኮሌጁ ስር ለሚገኙ ትምህርት ክፍሎች መምህራን እንዲሁም ለማስተርስና ለፒ ኤች ዲ ተማሪዎች ከግንቦት 25/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 5 ቀናት በአጼ ቴዎድሮስ ግቢ ድህረ ምረቃ ህንፃ የሶፍት ዌር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና ተሰጠ፡፡

የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ በመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከመሆኑ አንፃር ሶፍት ዌሮችን መጠቀም የምርምር ህትመት ለመስራት፣ የተሰበሰበውን ዳታ ለመተንተንና ለመተርጎም እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡

ኮሌጃችን የተለያዩ የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በተለያየ ጊዜ በተደጋጋሚ እየሰጠ እንደሚገኝ ይታዎቃል፡፡ በመሆኑም በስሩ የሚገኙትን ትምህርት ክፍሎች ውጤታማ ስራ ለማሰራት እንዲሁም የማስተርስና የፒ ኤች ዲ ተማሪዎች የመመረቂያ ጽሁፋቸውን ሲሰሩ የዳታ ትንተና ክፍተቶችን ለመሙላት ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን የተፈጥሮና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የድህረ ምረቃ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት አስተባባሪ ዶ/ር አጥናፉ ጓዴ ገልፀዋል፡፡




