“የመጀመሪያው የተሳካ የዳሌ አጥንት ስብራት ቀዶ ህክምና በውጪ በሚታሰር ብረት ተከናውኗል” ዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ
በጎንደር ዩኒቨርሲቲ አጠ/ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የአጥንት ቀዶ ህክምና ትምህርት ክፍል የመጀመሪያው የተሳካ ከፍተኛ የዳሌ አጥንት ስብራት ቀዶ ህክምና በውጪ በሚታሰር ብረት መከናወኑን የሆስፒታሉ ቀዶ ህክምና ት/ክፍል ባልደረባ የሆኑት ዶ/ር ቃለአብ ገልፀዋል።
በዶ/ር ቃለአብ ተስፋዬ በተመራ ቡድን ይህ መጀመሪያው የተሳካ ህክምና የተደረገው በመኪና አደጋ ምክንያት ከፍተኛ የዳሌ አጥንት ስብራትና ክፍተት ባጋጠማት አንዲት የአራት አመት ልጅ ነው፡፡ የዳሌ ስብራት ቀዶ ህክምናው በውጪ በሚታሰር ብረት የተሰራ ሲሆን “ህክምና የተደረገላት ልጅ በአሁኑ ሰአት በመልካም ሁኔታ ላይ ትገኛለች” ሲሉ ዶ/ር ቃለአብ ተናግረዋል። አክለውም ቀደም ሲል እንደዚህ አይነት በሽተኞች ተመሳሳይ ህክምና ለማግኘት ወደ አዲስ አበባ ሪፈር ተብለው ለተጨማሪ ወጭና እንግልት ይዳረጉ ነበር ብለዋል።



