
የፍልስፍና ዶክትሬት ድግሪ በተግባራዊ ሥነ-ልሳን ሀገር አቀፍ የካሪክለም ግምገማ ተካሄደ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል የፍልስፍና ዶክትሬት ድግሪ በተግባራዊ ሥነ-ልሳን / Doctor of Philosophy in Applied Linguistics/ ለመክፈት ሀገር አቀፍ ካሪኩለም ግምገማ በማራኪ አልሙኒዬም አዳራሽ ግንቦት 27 /2013 ዓ.ም አካሄደ ፡፡

በዕለቱ ሀገር አቀፍ የካሪክለም ግምገማውን በንግግር የከፈቱት የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዚዳንት ተወካይ ዶ/ር ብርቁ ደሞዝ በስምንት ኮሌጆች ፣ በሁለት ኢኒስቲቲዩቶችና በአንድ የትምህርት ክፍል በዩኒቨርሲቲያች እሰከ አሁን 29 የፒ ኤች ዲ ፕሮግራሞች ያሉን ሲሆን በማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ የእንግሊዝኛ ቋንቋና ስነ-ጽሑፍ ትምህርት ክፍል የፍልስፍና ዶክትሬት ድግሪ በተግባራዊ ሥነ-ልሳን መጨመሩ ዩኒቨርሲቲያችን የምርምር ዩኒቨርሲቲ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡
ዶ/ር ብርቁ አክለው እንደተናገሩት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰቡን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮችን ለመቅረፍ በየወቅቱ እያጠና የሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች አስፈላጊዎች በመሆናቸው ይህን ፕሮግራም ላዘጋጀው የትምህርት ክፍልና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው ብለዋል፡፡

በኮሌጁ መምህራን በዶ/ር ደርብ አቢው እና በዶ/ር አበበ አስረስ ለግምገማው መነሻ የሚሆን ፅሁፍ የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም በውጭ ገምጋሚዎች በዶ/ር ሩቂያ ሀሰን ከኮተቤ ሜትሮፖሊታኒያን ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ዶ/ር ቸሬ መስፍን ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አማካኝነት ውይይቱ እና ግምገማው ተካሂዷል፡፡




